ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰ/ሸ/ዞን/ከ/ፍ/ቤት የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2013 ዓ.ም በጀት ለስራ ዘመን አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- ሎት 2. ፈርኒቸር እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- ሎት 3. የጽዳት እቃዎች፣
- ሎት 4. ህትመት፣
- ሎት 5. የተዘጋጁ የደንብ ልብስ፣
- ሎት 6. የደንብ ልብስ 6000 ቲትረን፣
- ሎት 7. የፋይል መደርደሪያ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያላቸው።
- የግዥው መጠን ብር ከ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ /VAT/ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ የዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ / ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 20 /ሃያ ብር/ ብቻ በመክፈል ከፍ/ቤቱ መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው ውድድር በጥቅል መሆኑን እናሣውቃለን
- በጨረታ የሚሣተፍ ማንኛውም ተጫራች ውስጥ የተጠቀሱትን እቃዎች በሙሉ ዋጋ መስጠት ይኖርባቸዋል። ግን በከፊል ሞልቶ የቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
- የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሸ/ከ/አስ/ወ/ፍ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2/2 2013 ዓ.ም እስከ 20/2/2013 ዓ.ም 10፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ቴጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሸ/ከ/አስ/ወ/ፍ/ቤት በ23/2/2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንከ በተረጋገጠ CPO (ሲፒኦ) ከሆነ ኦርጅናሉን ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከፋይናንስ ወይም ዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ አስገብተው ማስያዝ አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጽ/ቤታችን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 664 03 47 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የሸዋ ሮቢት ከ/አስ/ወ/ፍርድ ቤት የግዥ ፋን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት