ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ገን/አካ/ኢኮ/ ትብብር ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- የጽህፈት መሳሪያ ግዢ፤
- የብትን ጨርቅ ግዢ ፤
- የጫማ ግዢ፤ የተዘጋጁ ልብሶች ግዢ
- የኤሌክትሮኒክስ እቃ ግዢ፤
- የስፖርት ቁሳቁስ ግዢ፤
- የጽዳት እቃ ግዢ፤ ሳይክልና የሳይክል መለዋወጫ ግገር፤
- የህንጻ መሳሪያ ግዢ፤ የፖሊቲንግ ቲዩብ ግዢ፤ የብሎኬት ግዢ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሣተፍ ይችላል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ያላቸው :
- የዕቃው መጠን 200,000.00 ብር በላይ ከሆነ የቫት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-3 የተጠቀሰትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በታሸገ ፖስታ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የዕቃው አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፌክሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል ከግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 26 የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጨረታ ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ( ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም ለኢንተርፕራይዞች ካደራጃቸው መስሪያቤት የዋስትና ደብዳቤ ማስያዝ ይጠበቅባቸወል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ገን/ኢኮ/ትብብር ጽ/ቤት ቁጥር 26 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ለእቃ አቅርቦት እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 26 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለእቃ አቅርቦት በአስራ ስድስተኛው ቀን 4:30 ይከፈታል::
- የጨረታ መከፈቻውን መዝጊያው ከመንግስት ስራ ቀን ውጪ ወይም በበዓል ቀን ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡ :
- ተጫራች ለወረቀትና የፐሪተር ቀለም መስሪያ ቤቱ ባስቀመጠው ናሙና መሰረት አውቃችሁ የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በምትመጡበት ጊዜ ናሙናውን እንድትመለከቱ እናሳውቃለን፡፡
- ውድድሩ በጥቅል/በሎት/ስለሆነ ተጫራቾች በከፊል መሙላት አይቻልም
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- መስሪያ ቤቱ የሚገዛቸውን እቃዎች የትራንስፖርትም ሆነ ሌሎች ወጪዎችን አይሸፍንም፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 26 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-664-0371/0336641336 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር
ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት