በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የሰሜን ሸዋ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ የሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ገን/አካ/ኢኮ/ትብብር ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- ሎት1.ተፋሰስ
- ሎት 2.የጎርፍ መከላከያ ግንብ
- ሎት 3. መሸጋገሪያ ድልድይ
- ሎት 4. ሼድ
- ሎት 5. አረንጓዴ ልማት
- ሎት 6.ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት7 የማሽነሪ ኪራይ
- ሎት 8.አዣራ ግዥ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሣተፍ ይችላል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ያላቸው
- የግንባታው መጠን 50,000.00 ብር በላይ ከሆነ የቫት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የዕቃው መጠን 200,000.00 ብር በላይ ከሆነ የቫት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ::
- ለዕቃ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ይዘጋና በዚያው ቀን በ4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ለግንባታው ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን 4፡00 ይዘጋና በዚያው ቀን በ4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በታሸገ ፖስታ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ::
- የዕቃው አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፌክሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለዕቃ ግዥ 100 ብር እና ለግንባታ ግዥ 300 ብር በመክፈል ከግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 26 የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ ::
- ተጫራቾች ለግንባታ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጨረታ ጠቅላላ ዋጋ 27384 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸወል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ገን/ኢኮ/ትብብር ጽ/ቤት ቁጥር 26 ለዕቃ ግዥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ለግንባታ ጨረታ እስከ 22ኛ ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4:00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ለእያንዳንዱ የግንባታ ስራ ኮስት ብሬክ ዳዎን ተሰርቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 26 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዕቃ በአስራ ስድሰተኛው ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ለግንባታ በ22ኛው ቀን 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ሰአት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻውንና መዝጊያው ከመንግስት ስራ ቀን ውጪ ወይም በበዓል ቀን ከዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል ::
- ውድድሩ በጥቅል/በሎት/ስለሆነ ተጫራቾች በከፊል መሙላት አይቻልም ::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- መስሪያ ቤቱ የሚገዛቸውን ዕቃዎች የትራንስፖርትም ሆነ ሌሎች ወጪዎችን አይሸፍንም፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 26 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-664-0371/0336641336 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት
[embedded content]