የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት በቤንች ሸኮ ዞን የሸኮ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች ለሚያሠራው መንገድ ከፈታ ሥራ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በኪራይ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ
ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተሰማሩበትን የሥራ ዘርፍ የሚገልፅ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር ) ያላቸዉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸዉ፡፡
- ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር የዓመቱን መድን ሽፋን ስለመግባታቸው የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ወይም ህጋዊ የኪራይ ዉል ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የመድን ሽፋን ወይም የዋስትና ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለማሽነሪ ከ2000 ዓ.ም ወዲህ የስሪት ዘመን ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር 30,000.00 (ሠላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ፣ በባንክ በተረጋገጠ ባንክ ጋራንቲ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ፣ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘዉን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል ከጽ/ቤቱ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይችላሉ፡፡
10. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሃሳብ ቴክኒክና ፋይናንሻል ዋና እና ኮፒ በማለት በአንድ ፖስታ ተፈርሞበት በጥንቃቄ ምንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያው ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት ለሸኮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 4 ለጨረታው በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ገቢ መደረግ አለበት፡፡
11. ጨረታው ማስተወቂያ በወጣው በ15ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
12. ይህ ጨረታ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0477780335
የሸኮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ሸኮ