የጨረታ ማስታወቂያ
የሸኖ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት በ2012 በጀት ዓመት በሸኖ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኘውን ደን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡–የደኑ ሽፋን በሄክታር (25.153) ነው ። ደኑን መሸጥ ስለምንፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች መጫረት ትችላላችሁ።
1ኛ. ተጫራቾች በዘረፉ ህጋዊ እና የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው ሆኖ የዘመኑን ግብር የከፈሉ በጨረታው መወዳደር ይቻላል፡፡
2ኛ ተጨማሪ እሴት ታክስ “VAT” የምዝገባ የምስክር ወረቀት፥ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN NO ያለው።
3ኛ ተጫራቾች ስለ ጨረታው ሙሉ ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት ቀናት/15/ ተከታታይ የስራ ቀናት የስራውን ዝርዝር መረጃውን በማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘውትር በስራ ሰዓት በሸኖ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት በመምጣት መግዛት ይቻላል።
4ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ብር 10,000/አስር ሺ ብር / በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
5ኛ. ተጫራቾች በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ፡- እስከ በ20/09/2012 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በዚሁ እለት በ20/09/2012 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት ይከፈታል
ማሳሰብያ፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ /አማራጭ/ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ 78 ኪሎ ሜትር ሸኖ ከተማ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡ የወረዳው የሸኖ ከተማ አስተዳደር ስልክ ቁጥር 0116870006/0116870122
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሸኖ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት