የሶዶ-ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ-አድራጎት ድርጅት በዘላቂ የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት ለአዴሌ-ጎሴ ቀበሌ ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ በዘርፉ ልምዱ ያላቸው እና ህጋዊ የሥራ ፈቃድ ያላቸው ሆነው ደረጃ WWC/GC-6 እና ከዚያ በላይ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

ሶዶ ቡኢ ህፃናትና ቤተሰብ ልማት በጎ-አድራጐት ድርጅት

Sodo Buee Child and Family Development Charitable Organization

የጨረታ ማስታወቂያ-በድጋሜ የወጣ

ለጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ(Deep Well Drilling Work)

የሶዶ-ቡኢ ህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ-አድራጎት ድርጅት በዘላቂ የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት ለአዴሌ-ጎሴ ቀበሌ ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ በዘርፉ ልምዱ ያላቸው እና ህጋዊ የሥራ ፈቃድ ያላቸው ሆነው ደረጃ WWC/GC-6 እና ከዚያ በላይ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል::

በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል::

  1. የጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ ልምድ ያለውና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
  2. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ::
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ /15% ቫት/ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉ::
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ ወይም ሲ.ፒ.ኦ የአጠቃላይ የጨረታ ዋጋውን 1% ማስያዝ የሚችሉ::
  5. አሸናፊው ተጫራች የተፈለገውን የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮና ኬዚንግ ተከላ ሥራውን በጥራትና በተፈለገዉ ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለማስረከብ የሚችል እና ለሚፈጸምለት የገንዘብ ክፍያ በተቋራጩ ሥም የታተመ ሕጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል።እንዲሁም በክፍያው ሂደት ተገቢው የመንግስት ታክስ ተቀናሽ ይሆናል::
  6. ተጫራቹ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት መጋቢት 07/2014 ዓ.ም ቀን ጀምሮ እስከ መጋቢት 14/2014 ዓ.ም በመደበኛ ክፍት የሥራ ቀናት ውስጥ አስፈላጊ የጨረታ ሰነዶችን ቡኢ ከተማ ከሚገኘው የድርጅታችን ጽ/ቤት በብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመውሰድ የተሟላ የጨረታ ሰነዱን በመደበኛ ክፍት የስራ ቀን (መጋቢት 14/2014 ዓ.ም) እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በኢንቨሎፕ ወይም ፖስታ አሽገው በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ::
  7. ጨረታዉ የሚከፈተዉ ተጫራች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸዉ በተገኙበት መጋቢት 14/2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይሆናል ::
  8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ፡-ሶዶ ቡኢ የህጻናትና ቤተሰብ ልማት በጎ-አድራጎት ድርጅት፣ ቡኢ ከተማ ሶዶ ወረዳ ጉራጌ ዞን ከአዲስ አበባ በስተ ደቡብ-ምዕራብ አቅጣጫ 103 ኪ.ሜ በአለምገና-ቡታጅራ-ሆሳና ዋናው አስፋልት መንገድ::

የስልክ ቁጥር፡ 046-8830023 ወይም 046-8880265 ወይም 0468830266

Bid closing date
Mar 23, 2022 2:00 PM

Bid opening date
Mar 23, 2022 2:30 PM

Published on

ሪፖርተር
(Mar 16, 2022)

ሪፖርተር
(Mar 16, 2022)

Bid document price
200.00 ብር

Bid bond
1%

Region

Bid closing date

Mar 23, 2022 2:00 PM

Bid opening date

Mar 23, 2022 2:30 PM

Published on

ሪፖርተር
(Mar 16, 2022)

ሪፖርተር
(Mar 16, 2022)

Bid document price
200.00 ብር

Bid bond
1%

Region

SNNPR

Water Construction

Water Well Drilling

Contract Administration and Supervision

Construction Machinery and Equipment

Sodo Buee Child and Family Development Charitable Organization

ሶዶ ቡኢ ህፃናትና ቤተሰብ ልማት በጎ-አድራጐት ድርጅት

Phone

+251 46 883 0350+251 46 883 0266+251 46 883 0265+251 46 883 0023