የታሸገ ውሃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር :JCC/NCB/WAT/11/13/20
1. የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን የታሸገ ውሃ ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
2. የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን የተጠቀሰውን የታሸገ ውሃ ግዥ ለማቅረብ ብቃት ያላችሁ ድርጅቶች በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነድ እንድታቀርቡ ተጋብዛችኋል።
3.ጨረታው የሚከናወነው በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት የመንግስት ግዥ አዋጅ በተገለጸው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ–ስርዓት መሠረት ይፈፀማል። የታሸገ ውሃ ግዥ ጨረታ የሚከናወነው ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች እና ከስራው ጋር አግባብነት ያለው ሆኖ የ2013 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው ፤ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽ ወቅታዊ ደብዳቤ ከአገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን፣ በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ካገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ዊብሳይት ላይ ፕሪንት አርጋችሁ እንዲሁም ቲን ሰርተፍኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችል ይሆናል። ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ በማጻፍና በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን በነጻ መውሰድ ይችላሉ።
4. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ከዚህ በታች በቁጥር 7(ሀ ) በተገለፀው አድራሻ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
5. የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ለ) በተገለጸው አድራሻ ጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይቻላል። የጨረታ ማስከበሪያው በተጫራቾች መመሪያ በተዘረዘረው መሰረት አያይዘው ያቀርባሉ። ዘግይተው የቀረቡ የጨረታው መልሶች ተቀባይነት የላቸውም። ጨረታው ጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ እለት በጨረታ ላይ ለመገኘት የፈለጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 7 (ሐ) በተጠቀሰው አድራሻ ጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7(ለ) በተገለጸው አድራሻ ጥር 3 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ 4፡00 ሰዓት ወይም በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ሰነዱን ማስገባት (በግዥ ክፍል ከጨረታ መክፈቻ ጊዜ በፊት በማቅረብ ይሆናል። ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አያይዘው ማቅረብ ኣለባቸው።
7. ሀ/ ሰነዶቹን የሚገዙበት አድራሻ የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ግዥ ፣ፋይናንስ፣ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ምድር ቤት፣ለ/ የጨረታ ሰነድ የሚገባበት አድራሻ የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ግዥ፣ ፋይናንስ፣ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ምድር ቤት፣ሐ/ ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ግዥ፣ፋይናንስ፣ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ምድር ቤት
8. የጨረታ ሰነዱን የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽነር ግዥ ፣ ፋይናንስ ፣ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30-6፡00 እና 7:30-11፡00 መግዛት ይችላሉ።
9. ድርጅታችን በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው።
አድራሻ:- የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ቦሌ መንገድ (አፍሪካ ጎዳና) ዲኤች ገዳ ህንፃ ጀርባ ግዥ ፣ፋይናንስ፣ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት
ስልክ ቁጥር 0116671792/0911992542
የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን