የጨረታ ማስታወቂያ
በፌ/ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሴቶች ማረ/ማረ/ማዕከል ከዚህ በታች የሚከተሉትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ውል ተዋውሎ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ጨረታ ቁጥር 1 የህንጻ መሳሪያዎችን በአንድ ጊዜ አጠቃሎ የሚያሰገባ ድርጅት
- ጨረታ ቁጥር 2- የፅዳት ዕቃዎች በአንድ ጊዜ አጠቃሎ የሚያስገባ ድርጅት
በዚሁ መሠረት፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በስራው መስክ ህጋዊነት ያለው የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ በገንዘብ ሚ/ር በእቃ ግዥና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ተጨማሪ እሴት ታክስ/Tin NUMBER/ ያላቸው የተሟላና ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ማስረጃ ሊያቀርቡ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለግንባታና ህንፃ መሳሪያዎች 10,000,00/አስር ሺህ ብር/ለፅዳት ዕቃዎች ብር 5,000.00/ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00/ ሃምሣ ብር/ቃሊቲ በሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሴቶች ማረሚያ ማረፊያ ማዕከል ስም በአካውንት ቁጥር 1000068020704 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከቢሮ ቁ. 10 መውሰድ ይችላሉ፡፡ መ/ቤታችን የሚገዛቸው እቃዎች ከተራ ቁጥር 1-2 የጨረታ ዝርዝር መመሪያ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ተካቶ ቀርቧል፡፡
- ተጫራቾች አንዱ በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው ዝርዝር ውስጥ ናሙናውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን / የመወዳደሪያ ሀሣባቸውን/ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናንሻልና ቴክኒካል በመለየት ናሙናቸውን ማቅረብ አለበት፡፡
- የግንባታና ህንፃ መሳሪያዎች እና የፅዳት እቃዎች እስከ ጥቅምት 30/2/2013 ዓም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት ይችላሉ ጨረታው በዕለቱ በ 4፡30 ሰዓት በመ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች የአሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሣቸው ትራንስፖርት ቃሊቲ በሚገኘው ሴቶች/ማረ/ማረ ማዕከል ዕቃ ግ/ቤት ድረስ አምጥተው ያስረከባሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114390404/0114394913/0118886411
አድራሻ፡– ቃሊቲ ክራውን ሆቴል ፊት ለፊት፣
የሴቶች ማረ/ማረ/ማዕከል