የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ከልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ማከራየት ይፈልጋል፡፡
- የጎማ እና የባትሪ ግዥ
- የህሙማን ኦክስጅን ግዥ
- የህንጻ ተገጣጣሚዎች ዕቃዎች ግዥ
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ
- ውሃ ዕቃዎች ግዥ
- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
- ካፍቴሪያ ኪራይ እና የህሙማን ምግብ አቅርቦት
ተጫራቾች
- ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- እንደ አስፈላጊነቱ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ/ች
- በመስኩ ሥራ የተሰማሩ
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለCPO 5000 ( አምስት ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸው፡፡ የጨረታ ሰነዱ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ግዥ ክፍል በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
የጨረታ ሰነድ በሰም ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ ለየብቻ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት ከ2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ግዥ ከፍል ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እንዲያስገቡ ሆኖ ጨረታው በዚህ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው በሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ተከፍቶ
- ውሳኔ ይሰጣል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ ዜደ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር 0462122371
በሲዳሚ ክልላዊ መንግስት የሀዋሳ
ከተማ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል