ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን በ2012 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ግዥ በየምድቦቹ ማለትም፡-
- ምድብ 1 የፅህፈት መሣሪያዎች
- ምድብ 2 ህትመት
- ምድብ 3 የፅዳት እቃዎች ምድብ
- ኤሌክትሮኒክስ ምድብ
- ፈርኒቸር ምድብ
- ቦርሣ
- ምድብ 7 የመኪና ጎማ
- ምድብ 8 የደንብ ልብስ
- ምድብ 9 የውሃ እቃ ምድብ
- የግንባታ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት መወዳደር የሚችል መሆኑን እየገለጽን፡-
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና በጀርባ ኮፒ የሆነ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቲን ያላቸው፣
- የሚያቀርቡት እቃ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ሙሉ አድራሻቸውን በድርጅቱ ስም የተዘጋጀ ማህተም መምታት አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ሰ/ሙ/ወ/ግ/ኢት/ጽ/ቤት ዋና ገንዘብ ያዥ የማይመለስ ብር 50 ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ/1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ይዘጋና በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰ/ሙ/ወ/ገ/ኢት/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በ16ኛው ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ባይገኝ የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉለው ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለተላለፉ ውሣኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃዎች በየፑሉ ማድረስ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ዋጋ ነው፡፡
- በማስታወቂያ ያልተገለጹ ካሉ በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
- ምድቡ ውስጥ የአንዱን እቃ ዋጋ ካል ሞሉ ከውድድር ውጭ ይደረጋሉ ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ሰ/ሙ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 140 1076 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት