የጨረታ ማስታወቂያ
የሰነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ ኤጀንሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ2o13 በጀት አመት የሚገለገልበትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ዝርዝራቸው ከዚህ ቀጥሎ የቀረበው ሰንጠረዥ በተገለፀው መሰረት CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
ተ/ቁ |
የጨረታው አይነት |
ናሙና እስፔስፊኬሽን /የሚቀርብበት |
የሚያስይዘት የ CPO መጠን |
1 |
ኣላቂ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ሎት1 |
እስፔስፊኬሽን / ናሙና /ይቀርባል |
5000
|
2 |
ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ሎት 2 |
እስፔስፊኬሸን ይቀርባል |
4000 |
3 |
ቋሚ የቢሮ እቃዎች /ፈርኒቸር እና ሌሎች የቤሮ እቃዎች/ግዥ ሎት 3 |
እስፔስፊኬሸን ይቀርባል
|
8000 |
4 |
የጥገና እቃዎች ሎት 4 |
ናሙና ይቀርባል |
2000 |
5 |
አላቂ የጽ/መሣሪያ ሎት 5 |
ናሙና ይቀርባል |
8000 |
6 |
አላቂ የጽዳት እቃዎች ሎት 6 |
ናሙና ይቀርባል |
5000
|
7 |
የደንብ ልብስ ሎት 7 |
ናሙና ይቀርባል |
1000 |
8 |
የመኪና እቃዎች ግዥ ሎት 8 |
ናሙና ይቀርባል |
4000 |
9 |
የተለያዩ ህትመቶች ሎት 9 |
እስፔስፊኬሸን ይቀርባል |
1500 |
10 |
የመኪና ጥገና ግዥ ሎት 10 |
እስፔስፊኬሸን ይቀርባል |
5000 |
11 |
ለቢሮ የሚሆን የህንፃ ኪራይ ሎት 11 |
የተባበሩት አደባባይ (አያት አደባባይ አካባቢ)
|
3000 |
12 |
ለቢሮ የሚሆን የህንፃ ኪራይ ሎት 12 |
ጎተራ ማሳለጫ አካባቢ |
3000 |
13 |
ለቢሮ የሚሆን የህንፃ ኪራይ ሎት 13 |
ከመገናኛእስከ ሳሊተ–ምህረት ያሉ አካባቢ |
3000 |
በዚህ ጨረታ መሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባችሁ ማስረጃ
- የንግድ ስራ ፈቃድ በዘመኑ የታደሰ፤ በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገበ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው፣ቲን ቁጥር ያለው ፣ በዘርፉ የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው፤ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ የታደሰ ያለው፤ የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ /ማስያዝ/ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለሎት1፣ለሎት2፣ለሎት3፣ለሎት 4፣ ለሎት5፣ለሎት6፣ለሎት7፣ለሎት8፣ ለሎት 9፣ ለሎት 10 እና ለሎት 11 የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር /በመክፈል ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመንጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኤጀንሲው የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 413 በመቅረብ ሰነዱን ገዝተው መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ የፌደራል ስነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በሚል በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በማሸግ የጨረታ ቁጥርና የእቃውን አይነት በግልጽ ፖስታው ላይ በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታው ሣጥን ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 413 ማስገባት አለባቸው
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ16ኛው የስራ ቀን በ5:00 ሰአት የጨረታው ሣጥን ተዘግቶ/ታሸጐ/ በ16ኛው ቀን በ5:30 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰአት ይከፈታል።
- ኤጀንሲው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ሜክሲኮ ጨለለቅ አልሳም ህንፃ 4ኛ ቢሮ ቁጥር 413
ስልክ ቁጥር፡-011-5-53-47-18/ 0115-58-9799
አዲስ አበባ
የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የግዥና
ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት