የጨረታ ማስታወቂያ
ያገለገለ እና ጥገና የሚፈልግ ተሸከርካሪ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ፡–
(SEDA) ሴዳ አንድ ያገለገለ እና ጥገና የሚፈልግ ላንድክሩዘር የ1991 እ.ኤ.አ ሞዴል የሆነ ተሽከርካሪ ባለበት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 50 በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ባህርዳር ቀበሌ 14 ሜድሮክ አካባቢ ከሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ በአካል በመገኘት መግዛት ይችላሉ ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማመልከቻቸውን ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ አምስት የስራ ቀናት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ከ10 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የማመልከቻ ቀን በተጠናቀቀ በማግስቱ ከጠዋቱ 4:00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– ስልክ ቁጥር 0911991462 ይደውሉ፡፡
ሰርብ ኢትዮጵያ ዲቨሎፕመንት አሶሴሽን