ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሰሜን ወሎ ዞን ገ/ኢ/ት መምሪያ ለራሱና አገልግሎት ለሚሰጣቸው የዞን መምሪያዎችና ተ/ጽ/ቤቶች
- ሎት 1 የጽ/መሣሪያዎች
- ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 3 ፈርኒቸር/የቢሮ ዕቃዎች/ የአገር ውስጥ
- ሎት 4 ፈርኒቸር/የቢሮ ዕቃዎች/ የውጭ
- ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት 6 የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች
- ሎት 7 የባዮ ጋዝ ማምረቻ መሣሪያዎች
- ሎት 8 የደንብ ልብስ
- 8.1የተለያዩ ጫማዎች
- 8.2 የተዘጋጁ ልብሶች
- 8.3 ብትን ጨርቅ
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ሙግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ለመሣተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያላቸው የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ማንኛውንም ዕቃ በኦርጅናል መሙላትና ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ወጭ የማጓጓዣ የማስጫኛ እና ማውረጃ እንዲሁም ወደ እስቶር የማስገባት ወጭዎችን በራሳቸው በመሸፈን በሰሜን ወሎ ዞን ግዥ ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል በተጨማሪም የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ የፎቶ ኮፒና የሩስክ ቀለሞች ኦርጅናል ስለመሆናቸው በሚወስደው ፕሪንተር ማስሞከር፤ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በባለሙያ ማስፈተሽ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ከ5 ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት መጥተው ውል መውሰድ እና በውሉ ላይ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ሁሉንም ያሸነፉትን ዕቃ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተም፣ ስምና ፊርማ በሚነበብ መልኩ መፃፍና በየገፁ ማህተም ማድረግና መፈረም ይጠበቅባቸዋል ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ማንኛውም የመንግስት ግብር እና ታክስን ያካተተ ዋጋ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ በየሎቱ ፖስታ አሽገው ማቅረብ እና በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ውድድሩ በድምር ዋጋ በሎት መሆኑ ታውቆ በየሎቱ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ለደንብ ልብስ ብትን/ጨርቅ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰሜን ወሎ ዞን ገ/ኢ/ትብብር መምሪያ ግዥና ንብ/አስተዳደር ቡድን በመምጣት የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመከፈል፤
- ከደንብ ልብስ ውጭ ከ እስከ 8 ላሉት ሎቶች ብር 100.00 /አንድ መቶ/ በመክፈል ገዝተው መውሰድ ይችላሉ
- ተጫራቾች ሎት 1-8 የሎትን የጨረታ ሰነድ መጫረቻ ሰነድ/ ከ22/4/2013 እስከ 7/5/2013 ዓ.ም ድረስ በመምጣት ገዝተው መወሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው ከሎት 1 እስከ ሎት 4 በ8/5/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ከሎት 5 እስከ ሎት 8 በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ሲሆን በጨረታው ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታው ተከፍቶ በግዥ መመሪያው ቁጥር 1/2003 መሰረት ተገዥ የመሆን /የመቀበል ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታው መክፈቻ ጊዜ ከ5 ቀን በፊት ለመምሪያው ማሳወቅ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1/ በመ/ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥ በኦርጂናሉን/ በጨረታ ፖስታው ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ ሙሉ በሙሉ ሳያስረክቡ ከፍያ ሲጠይቁ መ/ቤቱ እያስተናግድም ሙሉ በሙሉ እንዳስረከቡ ከፍያው ወዲያውኑ ይፈጸማል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማስረጃና የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም የተሳሳተ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል፡፡ በሕግም ያስጠይቃል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
- ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር-0333311597/2680 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
- ከሎት አንድም ሆነ ከአንድ ዕቃ በላይ ዋጋ ያልሰጠ ተጫራች ካለ ከጨረታ ውድድር ውጪ ያስደርጋል
- ሳምፕል ታይቶ ዋጋ የሚሞላቸው ዕቃዎች ዝርዝር በዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ ላይ በተገለጸው መሰረት የመ/ቤቱን ሳምፕል በማየት ዋጋ ሊሞላ ይገባል
በአብክመ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር
ቢሮ የሰሜን ወሱ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ
ትብብር መምሪያ