ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሰሜን ወሎ ዞን ማረ/ቤቶች መምሪያ /ወልድያ/ ከሃምሌ 1/2012 ዓ/ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ/ም ለ1 ዓመት የሚቆይ
- ሰርገኛ ጤፍ፣
- የተፈጨ ምጥን ሽሮ ፣
- የተፈጨ ምጥን በርበሬ፣
- የአተር ክክ ፣
- በቆሎ ፣
- እና ለማገዶ የሚሆን የተፈለጠ የባህር ዛፍ እንጨት የሚያቀርቡ ነጋዴዎች በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት ማኮናተር ይፈልጋል፡፡
በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በዚሁ የስራ መስክ ለመስራት የተመዘገቡ፣
- የሚሞላው ዋጋ ከብር 50 ሺህ በላይ ስለሆነ ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- ማስታወቂያው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከ24/09/2012 ዓ/ም እስከ 8/10/2012 ዓ/ም ድረስ 15 ተከታታይ ቀናት እስከ ድረስ ብቻ ነው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 1 በመቶ በጥሬ ወይም በሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከ24/09/2012 እስከ 8/10/12 ዓ/ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከመ/ቤቱ ዋና ገንዘብ ያዥ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ 9/10/12 ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን 9/10/12 ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ራሣቸው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች በሙሉ በራሣቸው ወጭ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ሙሉ አድራሻ፣ ማህተም ፊርማና ሌሎችን ማስረጃዎች አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታው የሚቀርቡ እቃዎች በሙሉ ጥራታቸው የጠበቀ መሆን አለበት፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራች ነጋዴዎች ለሚጫረቱበት ጨረታ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የበለጠ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 331 1240/0010 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሰሜን ወሎ ዞን ማ ረ/ቤቶች መምሪያ