የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር BG 016/2012
የሰላም ሚኒስቴር በ2012 በጀት አመት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ ለኩርሙክ ወረዳ አባዲ ቀበሌ ላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ለማስገንባት ላሰበው ግንባታ በደረጃ GC-5 ወይም BC-5 እና ከዚያ በላይ ያሉትን የሥራ ተቋራጮች አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው ፤
- የ2012 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፤
- የ2012 ዓ.ም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፤
- የ2012 ዓ.ም ውዝፍ ግብር ነፃ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችል ፤
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ተጫራች ለዚሁ የተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር በመከፈል ከሰላም ሚኒስቴር ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 305 በመቅረብ መግዛት ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዋስትና ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ዋጋው 2% (ሁለት በመቶ) ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ብቻ ከጨረታ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ግንባታውን የሚያከናውኑበትን ዋጋዶክመንት ዋናውንና ኮፒሁለት/2/እና ካምፓኒ ፕሮፋይል ዋናውንና ኮፒ ሁለት/2/ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በ16ኛ ቀን ከሰዓት 8፡00-8፡30 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አስገብተው በዚሁ ቀን በ8፡30 ሰዓት ላይ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በሰላም ሚኒስቴር ፋይናንስና ግዥ ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 305 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያስገቡት ዶክመንት ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ ለየብቻ መሆኑን እንዲያውቁት፡፡
- ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0115155546/ 0115517853 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሰላም ሚኒስቴር