ግልጽ የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል መስተዳደር በባሌ ዞን የሮቤ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ልማት ጽ/ቤት ለ2013 የበጀት ዓመት ለሮቤ ከተማ ሴክተር የመስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ፤
- የጽህፈት መሳሪያዎች ፣
- የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ቋሚ እና አላቂ እቃዎች፣
- የፅዳት እቃዎች፣
- ሞተሮች የተለያዩ
- የመኪና ጎማ እና መለዋወጫ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት የሚከተለውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር ከፍሎ ያጠናቀቀና ከገቢዎች ጽ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚመለከተው ከሆነ የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ዋናውንና ኮፒ በሠም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብር ሮቤ አገር ውስጥ ገቢ ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከሮቤ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ልማት ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ ፡፡
5. ተጫራቾች ኦርጅናል ሰነድ የማይመለስ ኮፒ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ጥራቱ የተረጋገጠ መሆኑን ማስረጃና በተጨማሪ ይጠቅመኛል የሚሏቸውን ማስረጃዎች ካሉ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
7. የኮምፒዩተሮች ቀለሞችን፣ ብእሮችን፤ቦርሳዎች ፤ የሰራተኞች ደንብ ልብስ እና ወረቀቶችን በተመለከተ ናሙና እና ጋራንቲ (የዋስትና ወረቀት) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎ ቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በአል ወይም