ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ ደቡብ ጐንደር አስተዳደር ዞን በሰዴ ሙጃ ወረዳ የሮቢት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ አገልግሎት መ/ቁ/ ግ/ጨ/02 ለ2013 በጀት አመት ለስልጠና፣ ለምዘና፣ የደንብ ልብስ፣ እና አስተዳደራዊ ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ ዕቃ
- ሎት 1 የጽዳት መሣሪያ፣
- ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣
- ሎት 3 የኤሌክትሪክ እና የህንፃ መሣሪያ፣
- ሎት 4 ጣውላና የጣውላ ውጤቶች፣
- ሎት 5 ብረታ ብረት ፣
- ሎት 6 ሲሚንቶና የስሚንቶ ውጤቶች፣
- ሎት7 የደንብ ልብስ ቆዳ ጫማና የፕላስቲክ ቦት ጫማ ውጤቶች፣
- ሎት 8 ህትመት፣
- ሎት 9 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈረቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳድር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በየዘርፉ ህጋዊ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፣
- የዘመኑ ግብር የከፈሉና ቲን ካርድ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከ50 ሺህ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፣
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ 50 ብር በየሎቱ በመክፈል ከመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ዘወትር በስራ ቀን መግዛት ይቻላል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1 በመቶ በጥሬ ገንዘብ /በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የከፈሉበትን ደረሰኝ ኮፒ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን እና ሌሎች መረጃወትን በፖስታ በማሸግ ይሀ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚታሽግበት ቀን እና ሰአት ድረስ ሰዴ ሙጃ ወረዳ ሮ/ቴ/ሙ/ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ለስራው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ይከፈታል፤
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ በድርጅቱ ስም የተዘጋጀ ማህተም እና አድራሻቸውነ ማስፈር አለባቸው፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑ ለወደፊቱም በመንግስት ጨረታ እንዳይሳተፉ የሚደረጉ መሆኑን እንገልፃለን፣
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም በዚህ ምክንያት ለሚከሰተው የተጫራቾች ወጭ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታውን ለመክፈት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸውን/ ቢገኙም ባይገኙም ለመክፈት አያስተጓጐልም፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በየአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተቀመጠው ሰአት ይሆናል፡
- ለበለጠ ማብራሪያ በሰ/ሙ/ወ/ሮ/ቴ/ሙ/ኮ/ግፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 በአካል ቀርበው ጠይቆ ወይም በስልክ ቁጥር 0581401273 ወይም 0920566597 ደውሎ መረዳት ይቻላል፡፡
- መ/ቤቱ ለእያንዳንዳቸው ዕቃዎች 20 የመጨመርና የመቀነስ ስልጣን አለው፡፡
- የዕቃዎች ርክክብ በተመለከተ አሸናፊው ድርጅት ሮ/ቴ/ሙ/ኮሌጅ ድረስ ማቅረብ በሙያተኛ እየተረጋገጠ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
ሮቢት ቴ/ሙ/ኮሌጅ