Cleaning and Janitorial Equipment and Service / Garments and Uniforms / Office Furniture / Office Machines and Accessories / Stationery / Textile

የሬደራል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የሬደራል ሠራተኛና ህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል፣

 1. አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች። (ሎት 1)
 2. ቋሚ የቢሮ እቃ (ሎት 2)
 3. የሠራተኞች የደንብ ልብሶች (ሎት 3)
 4. የቢሮ የጽዳት ዕቃዎች። (ሎት 4)

1. በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ የሚከተለውን ጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል

 1.  ዕቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ?ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ መሆን አለባቸው
 2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ 1% ሲፒኦ ወይም  በቼክ ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ አለባቸው።
 3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመከፈል የፌዴራል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
 4.  ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ 2.6 ኤንቨሎፕ (ፖስታ) ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን በመከተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳችሁን በሰም በታሸገ  ኤንቨሎፕ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ፣ ፋይናንሽያል ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ለይቶ በማሸግ እንደገና ደግሞ ቴከኒካሉን ብቻውን ፋይናንሽያሉን ብቻውን አሽጋችሁ በሰነዱ ላይ ስም፣ ሙሉ አድራሻ፣ ፊርማችሁንና ህጋዊ ማህተማችሁን ማስቀመጥ አለባችሁ። 2.8
 5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 4፡ 00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
 6.  ተጫራቾች የሚያቀርቡበት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል።
 7. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው አሸናፊው ድርጅት በጽሑፍ ከተገለፀ በኋላ ይሆናል።
 8. የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተሰጠው መሠረት የጨረታ አሸናፊነቱ በጹሑፍ እንደተገለጸ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ የፌዴራል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ውል መፈራረም አለበት። ይህ ሳይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥትገቢ ይሆናል።
 9. የዕቃዎች ርክክብ የሚካሄደው የፌዴራል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ይሆናል።
 10. የዕቃው ብዛት (Quantity) የሚወሰነው በመስሪያ ቤቱ (በድርጅቱ)የበጀት ሁኔታ ላይ ተመርኩዞ ነው
 11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ሆኖከበጀታችን በላይ የሚሆነውንመቀነስ ወይም መጨመር የምንችል መሆኑን እንገልጻለን።

2.የ ተጫራቾች መመሪያ

2.1 የዘመኑ ግብር ከፍሎ ማጠናቀቁን ከሀገር ውስጥ ገቢ መሥሪያ ቤት ማስረጃ በእጅ ማቅረብ አለበት።

2.2ተጫራቾች በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገብና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል።

2.3 ተጫራቹ የዘርፉን የንግድ ፍቃድ ኦርጅናሉንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ አለበት።

2.4 ማንኛውም ተጫራች የንግድ ፍቃድ ከሚፈቅድለት ዘርፍ ውጪ መጫረት አይችልም።

2.5 በዋጋ አጻጻፍተራ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ የተደለዘው (የተሰረዘው) ዋጋ ተቀባይነት የለውም (አይኖረውም)።

2.6 በእርሳስ እና ቀለም በሚጠጣ ብዕር እንዲሁም ከተሰጠው ቦታ ውጪ የተጻፈ ዋጋ ተቀባይነት የለውም (አይኖረውም)

2.7 የተጫራቹ ሙሉ ስም ፊርማ የድርጅቱ ቲተርና ማህተም የሌለው ሠነድ ተቀባይነት የለውም።

2.8 አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ የማጓጓዣ ወጪ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

2.9 አሸናፊ ተጫራች የዕቃዎቹን ናሙና አቅርቦ ማሣየት አለበት።

2.10 ተጫራቹ የዕቃዎቹን ነጠላ ዋጋ በማያሻማ ሁኔታ ከመግለጽ ውጪ እንዲሁም ከተሰጡት የዕቃ ስም ዝርዝሮችም ሆነ ያዕቃዎቹን መለኪያዎች ለውጦ (ቀይሮ) መጻፍ አይቻልም።

2.11 ተጫራች የዕቃዎቹን ዋጋ ከዚህ ሠነድ ውጪ በሌላ ዋጋ መስጫ ላይ ሞልቶ መመለስ አይችልም።

2.12 ተጫራቹ የሀገሪቱን የፌዴራል አዋጆችና ደንቦችን የማክበርና በዕቃ አቅርቦት ወቅት የሚቀርበውን የውል ሰነድ መፈረም ይኖርበታል።

2.13 ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረበው ዋጋ የማሻሻያ ሃሣብ የማቅረብና ራሱን ከጨረታው ማግለል አይችልም።

2.14 አሸናፊ ተጫራች ለእያንዳንዱ ዕቃ የሰጠው ነጠላ ዋጋ እስከ 30/10/2013 ዓ.ም ድረስ ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን አውቆ ጽ/ቤቱ ተጨማሪ የግዢ ጥያቄ ፍላጐት ባቀረበበት ወቅት ለማቅረብ ፍላጐት ያለውና ለማቅረብ ውል መፈፀም የሚችል መሆን አለበት።

2.15 አሸናፊ ተጫራች ሚንስቴር መ/ቤቱ ከሚያደርገው የግዢ ውል 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት የሚችል መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል።

2.16 አሸናፊ ተጫራች ክፍያ የሚፈፅምለት ዕቃዎቹን ገቢ አድርጐ ሲያጠናቅቅ ይሆናል።

2.17 ተጫራች በማንኛውም ሁኔታ የጨረታውን አካሄድ ሥነ-ሥርዓት ለማስቀየርም ሆነ ለማሣሣት ከሞከረ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ተደርጎ ወደ ፊት በሚወጣው የጨረታ ማስታወቂያ ላይ እንዳይሣተፍ ይደረጋል።

2.18 ማንኛውም ተጫራች ለሚያቀርባቸው የዕቃ ዋጋዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ማካተቱንና አለማካተቱን መግለጽ ይኖርበታል።

2.19 መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- መረጃ በስልክ ቁጥር፡-09-11-1634-77/ 0911-17-97-77

ወይም 011-5154335 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የፌዴራል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር