የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን የሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 በወረዳው ውስጥ ላሉ ሴክተሮች የተለያዩ እቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።
በዚሁ መሰረት ፡-
- በ2013 ዓ.ም በበጀት ዓመት አላቂና ቋሚ የጽ/ቤት መሳሪያዎችን ፤ኤሌክትሮኒክስ፤
- የተለያዩ ጎማዎችን እና
- የተለያዩ የደንብ ልብሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ በተጠቀሱት የንግድ ሥራ ዘርፎች ሕጋዊ የሆናችሁ ድርጅቶች እንድትሳተፉ እንጋብዛለን፡፡
ተሳታፊዎች
- ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ እና የዓመቱን ግብር የከፈሉ ዋናና ቅጅ መረጃ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡበትን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በጨረታ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ከሙስናና ከብዝበዛ ድርጊት የፀዱ መሆን አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪው (ዋ) ጨረታውን ለማሰናከል ከሞከሩ ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ። ለወደፊትም በመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ አይሳተፉም ፣ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብም አይመለስም።
- በኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢዎች የተረጋገጠ ዕቃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት ።
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ ከተከፈተ በኋላ በሰነዱ ላይ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ መለወጥ ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታ መውጣት አይችልም፡፡
- ተወዳዳሪዎች በጨረታው ላይ መግለጫ ወይም የማሻሻያ ጥያቄ ካላቸው በተመዘገቡ በአምስት (5)ቀን ውስጥ ማቅረብ ይችላሉ።
- ተወዳዳሪዎች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስም ፊርማ እና አድራሻ መጥቀስ አለባቸው።
- ተወዳዳሪዎች በጨረታው አካሄድ ቅሬታ ካላቸው ለሚመለከተው ክፍል ማቅረብ ይችላሉ።
- የጨረታው ሰነድ በሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ቁጥር 7 የማይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ ) በመክፈል ማግኘት ይቻላል፡፡
- ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10( አስር ቀን ) ተከታታይ የሥራ ቀናት የሰነድ ሽያጭ ይከናወናል።
- የጨረታ ሰነድ የማሰረከቢያ የመጨረሻ ቀን 19/3/2013 ይሆናል።
- የጨረታ ሰነድ አቅራቢ ድርጅቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ20/3/2013 ይከፈታል ።
- ግዥ የሚፈፅመው አካል ጨረታውን በከፊልም ሆነ በጥቅል የመሰረዝ መብት አለው።
❖ በተጨማሪም በዚህ ያልተካተቱትን የጨረታው ደንቦች እና መመሪያዎች በሚገዙት የጨረታው ሰነድ ላይ የሰፈረ ስለሆነ የበለጠ መረዳት የምትችሉ መሆኑን በትህትና እንገልፃለን።
በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን የሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት