ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሞጣ ከተማ አስ/ጤ/ጥ/ጽ/ቤት ለሞጣ ጤና አጠ/ጣቢያ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ
- ሎት 1 ህትመቶች በግልጽ ጨረታ አወዳዳሮ ለማሣተም ይፈልጋል
- ሎት 2 ጀኔሬተር መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የህትመቶች እና የጀኔሬተሩን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሞጣ ጤ/አጠ/ጣቢያ ብር 30 የማይመለስ በመክፈል ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሞ/ጤ/አጠ/ጣቢያ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 በ16ኛው ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጤና ጣቢያው 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት ወይም በጠቅላላ ዋጋ ድምር ይሆናል፡፡
- አሸናፊው የህትመት ውጤቶችን እና ጀኔሬተሩን አጓጉዞ ጤና ጣቢያ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 6610002 ወይም 0910076312 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
የሞጣ ከተማ አስ/ጤ/ጥ/ጽ/ቤት