ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የሊዝ የጨረታ ማስታወቂያ
- የሞጣ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለመኖሪያና ንግድ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል:: በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ በማይመለስ 250 ብር በመክፈል ሞጣ ከተማ አስ/ከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሣውቃለን::
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል::
- የጨረታ ሣጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል::
- ቦታውን መጐብኘት ለሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም በውስጥ ማስታወቂያ የምናሣውቅ ይሆናል::
- ስለጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይቻላሉ::
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 በከተማ አስተዳደሩ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል:: 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል::
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚመለሰው የጨረታ አሸናፊው ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ይሆናል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናና የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት ከ10 በመቶ ያላነሰ በዝግ አካውንት በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት/ሲፒኦ/ ሰነድ ከዋጋ እና ከሃሣብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል::
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊልም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ 058 6612040/0586611440 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::
የሞጣ ከተማ አስ/ከ/ል/ቤ/ኮን/አገ/ጽ/ቤት