አስችኳይ የጨረታ ማስታወቂያ
የሞኤንኮ ሠራተኞች ማህበር ያገለገሉ የመኪና እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ጨረታውን መጫረት የሚፈልግ ተጫራች ከረቡዕ መስከረም 27 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ዓርብ መስከረም 29 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 – 10:00 ሰዓት እና ቅዳሜ መስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ከ2:00 – 3:30 ሰዓት የጨረታውን ሰነድ ሞኤንኮ ሠራተኞች ማህበር ጽ/ቤት በመምጣት የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከፍሎ በመግዛት እቃውን ባለበት ሁኔታ መመልከትና ጨረታውን መወዳደር የሚችል መሆኑን እየገለጽን ጨረታው ቅዳሜ መስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ከረፋዱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
የሞኤንኮ ሠራተኞች በማህበር
አድራሻ፡
ቦሌ ሐያት ሆስፒታል አጠገብ
በተጨማሪ ሙሉ መረጃ በሰነዱ ላይ ተገልጿል።