ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የምድረ ገነት ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት
- ሎት አንድ የጽህፈት መሣሪያ
- ሎት ሁለት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የም ትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በስራ ዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣
- ቲን ናምበር የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፣
- የግዡ መጠን ከ50 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆኑ ማስረጃ የሚያቀርብ ፣
- አሸናፊ ድርጅት የተጠየቀውን ማቴሪያል በራሱ ወጭ ከተማ አስተዳደሩ ድረስ ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት ከቢሮ ቁጥር 2 የማይመለስ ብር 50 በመክፈል የጨረታ ሰነዱ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ጋር በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጨረታ ከወጣበት ለተከታታይ 16 ቀን እስከ 4፡00 ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሣጥኑ ጨረታ ከወጣበት በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጐ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ላይ መፈረምና ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ከጠቅላላው ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከከተማ አስተዳደሩ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ የገቢ ህጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመስሪያ ቤቱ ሰነድ በሌላ ሰነድ መቀየር ወይም በዋጋው ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ የለበትም፡፡ አጋጣሚ ስርዝ ካለው ፊርማ መኖር አለበት፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን አንስቶ 40 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሎት/በተናጠል/ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የወሰዱትን የተጫራቾች መመሪያ ማህተም በማድረግ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ምድረ ገነት ከተማ አስ/ገ/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0918805116 ወይም 0929070328 ቁጥር ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
የምድረ ገነት ከተማ አስ ተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት