Construction Machinery / Construction Machinery and Equipment / Machinery and Equipment / Others / Vehicle

የምዕ/ጐ/ዞን የቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለቡሬ ዙሪያ ለመንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት ግሬደር፣ 16 ሜ.ኩ የሚጭን ገልባጭ መኪና ፣ ሮለር፣ ሎደር፣ ዶዘር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈለጋል

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የምዕ/ጐ/ዞን የቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለቡሬ ዙሪያ ለመንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ ገጠር ቀበሌዎች ለመንገድ ሥራ አገልግሎት የሚውል ማሽን ኪራይ ነዳጅና ማጓጓዣ ትራንስፖርት አከራይ ድርጅቱ ችሎ

 • 1ኛ.ግሬደር፣
 • 2ኛ. 16 ሜ.ኩ የሚጭን ገልባጭ መኪና ፣
 • 3ኛ ሮለር፣
 • 4ኛ.ሎደር፣ 5ኛ. ዶዘር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈለጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን

መስፈርቶች የምትሟሉ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 1. ከዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ያላቸው
 3. ተጫራቾች የሞሉት ጠቅላላ ብር 200 ሺህ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 4. ተጫራቾች በጨረታውለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ/1 ቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት ዋና ገ/ያዥ ላይ በመክፈልና የከፈሉበትን ማስረጃ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ አሸገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. የማሽን ኪራይ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16/04/2013 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡
 7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዛት ሲመጡ የንግድ ሥራ ፈቃዳቸውን/ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ የጨረታ ሰነድ ለሚሸጠው አካል ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡
 8. አሸናፊው ተጫራቾች የሚመረጠው ባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ድምር ነው፡፡ ሁሉንም ወይም አምስቱን የማሽን ኪራይ ዋጋ ማቅረቢያ ላይ መሞላት አለበት ይህ ካልሆነ ግን ሙሉ በሙሉ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡ የሞሉትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ከቫት ውጭ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ካልሆነ ግን የተሞላው ዋጋ ቫትን እንደሚጨምር ተደርጐ ይወስዳል፡፡
 9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ 100 ብር በመክፈል ከቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ማግኘት ይችላሉ፡፡
 10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 11. ተጫራቾች ዋጋ በሚያስቀምጡበት ጊዜ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ ከሁሉም የጨረታ ሰነዶች እና ፖስታው ላይ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል እንዲሁም የሞሉትን ዋጋ ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ መሆን የለበትም ሆኖም ግን ስርዝ ድልዝ ካለው ፊት ለፊት ፖራፍ ወይም መፈረም ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ለማየት እና ለመነበብ አዳጋች ከሆነ ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ ከጨረታ ውጭ ይደረጋል፡፡
 12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መግለጫ ቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 774 02 37 መረጃ ማግኘት ይችላል፡፡
 13. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 ዓ.ም መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
 14.  አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡

የቡሬ ዙሪያ ወረዳ ግዥና ንብ/አስ/ቡድን