ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁ. WMWD AIG 01/2013
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የምዕ/ሸዋ ዞን ኢሉ ገላን ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ
- የተለያዩ ቋሚና አላቂ
- የጽህፈት መሳሪያዎች ፣
- የጽዳት ፣
- አላቂ የቢሮ እቃዎች ፣
- የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች ፣
- ሞተር ሳይክል ፣
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣
- የደንብ ልብሶች እና የመሳሰሉ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል ::
- የጨረታው ተወዳዳሪዎች የ2012 ዓ.ም ንግድ ፈቃዳቸውን ያደሱና የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ከሆኑ ማስረጃውን በፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የጨረታው ተወዳዳሪዎች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎችን ጠቅላላ ዋጋ ድምር 1(አንድ)% ብር በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ(CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል ::
- ተጫራቾች የዕቃዎችን ዓይነትና ብዛት የሚገልጽ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ የተዘጋጀ ሰነድ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ) ብር በመክፈል በኢሉ ገላን ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ገዝተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋና እና ኮፒውን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በመግዛት በ16ኛው በስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ውሉን ሲፈርሙ ካሸነፉት ብር የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ 10% ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን ዕቃዎች በራሳቸው ማጓጓዣ/ ወጪ/ በወረዳው ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ግምጃ ቤት ኢጃጂ ከተማ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻችን፡– በነቀምት መስመር ከአዲስ አበባ 200 ኪሜ ርቀት አስፋልት መንገድ ላይ እንገኛለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር በሞባይል 0913160553/0913144073/በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
የምዕ/ሸዋ ዞን ኢሉ ገላን ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት