የጨረታ ማስታወቂያ
የምዕራብ ወለጋ ዞን መነሲቡ መንዲ ሆስፒታል በ2013 በጀት ዓመት ለሆስፒታል የሚያገለግሉ
- የህትመት ውጤቶች
- የህክምና መገልገያ መድኃኒቶችና ሪኤጀንቶች አዋዳድረን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- የ2013 በጀት ዓመት ግብር የከፈለ እና የንግድ ፍቃድ ያደሰ
- ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው
- ቲን ቁጥር ያለው (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ
- በአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያለው
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ባሉት 15(አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀኖች የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመከፈል የጨረታውን ሠነድ ከመንድ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላል
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ከ05/02/2013 ዓ.ም እስከ 20/2/2013 ዓ.ም እስከ 11:30 ሰዓት ከፍት ሆኖ በ23/02/2013 ዓም በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች የማጓጓዝ የመጫኛና የማውረጃ ወጪ በመቻል ጽ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ለአሽናፊው ክፍያ የሚፈጸመው ዕቃዎቹ ሙሉ በሙሉ ንብረት ክፍል ገቢ ሲሆን ብቻ ነው፡፡
- ተጫራቹ በተገለጸው በእስፔስፍኬሽን መሠረት ጨረታውን ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለጸበት ከ5ኛው ቀን በኋላ በቀጣዮቹ 5 ቀናት ውስጥ መ/ቤት ቀርቦ ውል መፈራረም ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በምዕራብ ወለጋ ዞን መንድ ሆስፒታል :: የሞባይል ቁጥር 090105707/0935885882 በመደወል መጠይቅ ይችላሉ፡፡
በምዕራብ ወለጋ ዞን መንዲ ሆስፒታል