ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ሜኤኒት ጎልዲያ ወረዳ ባቹማ ከተማ በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ሊያሰራ ላሰበው የኮላይ ቀሪ የጤና ጣቢያ ግንባታ ስራ ይህንን ለብሔራዊ በግልጽ ጨረታ በማውጣት ተጫራቾችን ጥሪ ማድረግ ይፈልጋል
በዚህ መሰረት እንደሚከተለው አስቀምጧል፡፡
ልዩ ስሙ 1 የኮላይ ቀበሌ 2 ፣ባዙን ዜማ ቀበሌ በሁለቱም ቀበሌዎች ቀሪ የጤና ጣቢያ ግንባታ ስራ መሠራት የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተቀመጡትን የመወዳደሪያ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በኮንስትራከሽን በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ደረጃ 6/GC/BC እና ከዛ በላይ የሆነ ::
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት በሚመጣበት ጊዜ ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል የንግድ ፍቃድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት የቫት ተመዝጋቢ ስርተፊኬት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ዋናውን በማቅረብ የምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይናስ መምሪያ የጨረታ ኮሚቴ ቢሮ ቁጥር 03 የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር ብቻ በመክፈል መግዛት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በአቅራቢነት የምስክር ወረቀት እና ከግብር ነፃ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000/ ሀምሳ ሺህ ብር / በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የገዙትን ሠነድ (ፋይናንሻል እና ቴክኒካል) ከላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች ለእያንዳንዳቸው 1(አንድ) ኦርጅናልና 2 (ሁለት) ኮፒ በማድረግ በፖስታ በሰም በታሸገ ፖስታ በማቅረብ (ፋይናንሻል እና ቴክኒካል) ዶክመንት በጥቅሉ በአንድ ፖስታ መታሸግ አለባቸው ::
- እያንዳንዱፖስታ በሰም በታሸገ ፖስታ ማህተም መምታት እና መፈረም አለበት ::
- ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ ማቅረቢያ ሠነዶች ላይ ተጫራቾት ህጋዊ ወኪል ፈርማ እና እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መኖር ኣለበት ::
- እያንዳንዱ ፖስታ የሚወዳደሩበት የስራ ቦታ የሎት ቁጥር የተቋራጩ አድራሻ እና የተወካዩ ስልክ ቁጥር በመግለጽ መጻፍ አለበት ፡፡
- ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ቴክኒካል 1 (አንድ) ኦርጅናልና (አንድ) ኮፒ ፋይናሻል ዶክመንት 1(አንድ) ኦርጅናልና 2 (ሁለት) ኮፒ በማድረግ ማስገባት አለባቸው ::
- ጨረታ የሚታሸገው ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን ወይም አስራ ስድስተኛው ቀን የበዓል ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚውል ሆኖ የምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይ/ኢኮ/ል/መምሪያ የጨረታ ኮሚቴ ቢሮ ቁጥር 03 ከጠዋቱ 4(አራት ሰዓት) ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይታሸጋል ::
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን ወይም አስራ ስድስተኛ ቀን የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚውል ሆኖ የምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይ/ኢኮ/ል/መምሪያ የጨረታ ኮሚቴ ቢሮ ቁጥር 03 ከሰዓት 8፣00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡– ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 0916154317/097598 6389/ 0912368800/ 0910125033
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/የምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
ጀሙ