Construction Machinery / Construction Machinery and Equipment / Machinery and Equipment

የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት አማካኝነት ለምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ከአ.ብ.ክ.መ አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባባሪያ ኮሚሽን ጽ/ቤት ባገኘው የበጀት ድጋፍ በድርማ ወንዝ ቆላድባ ከተማ፣ገበባ ሳልጅ ቀበሌ፣ጉራባ ባታ/ቀበሌ፣ጃንጓ ቀበሌ እና ሰራባ ዳብሎ ቀበሌ የጎርፍ መከላከያ ስራ ኤክስካቫተር ተከራይቶ ለማሰራት ይፈልጋል

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት አማካኝነት ለምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ከአ.ብ.ክ.መ አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባባሪያ ኮሚሽን ጽ/ቤት በአገኘው የበጀት ድጋፍ በድርማ ወንዝ ቆላድባ ከተማ፣ገበባ ሳልጅ ቀበሌ፣ጉራባ ባታ/ቀበሌ፣ጃንጓ ቀበሌ እና ሰራባ ዳብሎ ቀበሌ የጎርፍ መከላከያ ስራ ኤክስካቫተር ተከራይቶ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

 1. የዘመኑ የ2012 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ፣
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ / ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ፣
 3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ዋናዉንና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 4. የጨረታ ሰነዱን 100/አንድ መቶ ብር /በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
 5.  የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትፈልጉ ከ26/08/2012 ዓ/ም ጀምሮ ምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ደ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ዘወትር በሥራ ስዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
 6. የምንከራየው እስካቫተር እና ሎቤድ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን አሸናፊዉ የሚለየዉ በሎት ድምር በቀረበዉ ዝቅተኛ ዋጋ ይሆናል ፡፡
 7. ተጫቾች የጨረታ ሰነዱን በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ከ26/08/2012 ዓ.ም እስከ 10/09/2012 ዓ/ም ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ማግነት ይችላሉ፡፡
 8.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ / ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፖስታዉ ታሽጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
 9.  በጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት 11/09/2012 ዓ/ም በ3፡30 ታሽጎ በግዥ፤ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በዚሁ ቀን 11/09/2012 ዓ.ም በ4.00 ይከፈታል፡፡
 10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በለሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፍት ስልጣን አለዉ፡፡
 11.  የኤክስካቫተሩ ዓይነት ባለሰንሰለት ሆኖ የፈረስ ጉልበቱ 197 እና ከዚያ በላይ ያለው መሆን አለበት፣የሎቤድ ኪራይ ቦታው ድረስ/ድርማ ወንዝ ቆላድባ ከተማ፣ገበባ ሳልጅ ቀበሌ፣ጉ/ባታ፣ጃንጓ ቀበሌ እና ሰራባ ዳብሎ ቀበሌ ድርስ ሆኖ የመወሰጃና የመመለሻ በአሸናፊው ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ዋጋው የሚሞላው ነዳጅን ጨምሮ መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ ወይም ነዳጅ በአሸናፊው ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፡
 12. አሸናፊው ተጫራች ሁለት እስካቫተር እና ከዚያ በላይ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡
 13.  ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
 14.  ማንኛዉም ተጫራቾች /ተወዳዳሪ/ አሸናፊነቱ ተገልጾለት ዉል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ቀናት ዉስጥ የአሸነፉበትን የማሽን ኪራይ ወይም አገልግሎት በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አማካኝነት እስከ ስራ ቦታው ማሽኑን በማቅረብ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
 15. በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583350601 ወይም 0918739006 በመደወል ማግኘት ይችላሉ

ማሳሰቢያ ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከትም ፤

የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት