Vehicle (garage service)

የምስራቅ ሸዋ ዞን ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የመንግስት መኪናዎችን ለማስጠገን ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ 

የምስራቅ ሸዋ ዞን ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በዞኑ ለሚገኙ ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚያገለግል በአዳማ ከተማ ብቻ የሚገኙ ጋራዦችን የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የመንግስት መኪናዎችን ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል። 

 1. ተጫራቶች በጨረታው ለመካፈል ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ሆኖ ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። 
 2. ተጫራቾች የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው ሆኖ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። 
 3. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፀውን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይቻልም። 
 4. ተጫራቶች በጨረታው ለመካፈል የዞኑ የመንግስት መኪኖች የሚገኙት በአዳማ ከተማ ስለሆነ ማንኛውም በመኪና ጥገና ጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልግ ድርጅት የድርጅታቸው (ጋራዥቸው) አድራሻ በአዳማ ከተማ ውስጥ ብቻ መሆን እንዳለበት እና ከአዳማ ከተማ ውጪ ያሉ መወዳደር የማይችሉ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል። 
 5. ተጫራቶች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠውን ማንኛውንም ሁኔታዎች በጥሞና እና በጥንቃቄ አንብበው የጨረታ ሰነዱን መሙላት ይኖርባቸዋል።ይህ ሳይሆን ሲቀር ለሚፈጠረው ማንኛውም ስህተት ኃላፊነቱ የተጫራቹ ድርጅት ይሆናል። 
 6. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስሙን እና ሙሉ አድራሻውን በትክክል ገልጾ የድርጅቱን ማህተም አድርጐ በጨረታ ሰነዱ ላይ ፈርሞ የቴክኒኩን የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን በተናጠል በፖስታ አሽጐ ማቅረብ ይኖርበታል። እንዲሁም ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስሙንና ሙሉ አድራሻውን በትክክል ገልጾ የድርጅታቸውን ማህተም አድርገው በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ፈርመው የፋይናንሱን የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን በተናጠል በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። 
 7. የጨረታው አከፋፈት የሚካሄደው በቅድሚያ የቴክኒክ ኦርጅናል ሰነዱ ይከፈትና የቴክኒክ ግምገማ ውጤት እንዳለቀ የቴክኒኩን ግምገማ ያለፉ ተጫራቾች የፋይናንስ ኦርጅናል ሰነዳቸው የሚከፈት ሲሆን የቴክኒክ ግምገማውን ያላለፉ ተጫራቶች የፋይናንስ ሰነዳቸው የማይከፈት መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል። 
 8. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 (አምስት ሺህ) CPO ማስያዝ ይኖርበታል። በጨረታው የተሸነፉትም ተሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት ይመለስላቸዋል። 
 9. ተጫራቾች የስራ ብቃታቸውን የሚገልፅ የድርጅታቸውን ፕሮፋይል (company profile)፡ የሠራተኞቻቸውን የትምህርት ማስረጃ እንዲሁም የተጠየቁትን ሌሎች ማስረጃዎች በሙሉ ኮፒውን ከቴክኒክ ኦርጂናል እና ከቴክኒክ ኮፒ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ፖስታው ውስጥ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። 
 10. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በምስራቅ ሸዋ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 15 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ። 
 11. ጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 1፡30 ይሸጥና ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ሰነዱ መሸጥ ከጀመረበት ቀን ጀምሮ እስከ (16) አስራ ስድስተኛው የስራ ቀን እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ አስገብቶ በ6፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ማለትም በአስራ ስድስተኛው (16) የስራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም በጨረታው ለመካፈል የፈለጉ ማናቸውም’ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 
 12. የጨረታው ውድድር የሚካሄደው ቴክኒክን በተመለከተ ለእያንዳንዱ ስራ የሚሰጠው ነጥብ ጠቅላላ ድምር ሲሆን የዋጋ ማቅረቢያ (Finance) በተመለከተ ለእያንዳንዱ ስራ የሚሰጠው ዋጋ ተደምሮ ጠቅላላ ድምር ይሆናል። 
 13. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ እና የቴክኒከ ይዘት ሙሉ በሙሉ መረዳት ይኖርባቸዋል። 
 14. ከቀረቡ ተወዳዳሪዎች መካከል በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ከጽ/ቤቱ ጋር ለአንድ ዓመት የሚቆይ ውል የሚፈራረም ሆኖ ዋጋውም ለአንድ አመት ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል። 
 15. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በግልፅ መፃፍ አለበት። 
 16. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበትን የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ ነጠላ ዋጋ (የአንዱ ዋጋ) ማቅረብ ይኖርበታል። 
 17. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርባቸውን የመኪና ጥገናዎች የቴክኒክ ግምገማውን ተጫራቹ በጨረታ ሰነዱ ላይ ያቀረበውን የቴክኒከ የጨረታ ሰነድ ላይ በመመርኮዝ የቴክኒክ ኮሚቴው ድርጅቱ (ሀራጁ) በሚገኝበት ቦታ በአካል ተገኝቶ በቴክኒከ ጨረታ ሰነድ ላይ የቀረበውን ለማረጋገጥ የሚገመግም መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል ። 
 18. ማንኛውም ተጫራች የፋይናንስ ዋጋም ሆነ የቴክኒክ ይዘት የምስራቅ ሸዋ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ መሙላት ይኖርበታል። 
 19. ከዚህ በላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ባይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈፅሙ ሲቀሩ በመንግስት የግዥ መመሪያ ቁጥር 02/2004 እና FA 1/2009 በአዋጅ ቁጥር 157/2002 መሠረት ጽ/ቤቱ እርምጃ መውሰድ የሚችል መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል። 
 20. ማንኛውም ተጫራች ለድርጅቱ ባለጋራዥ ዋስትና የሚሆን ህጋዊ የኢንሹራንስ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል። 
 21. አሸናፊው ድርጅት የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ ጨረታን ማሽነፉ ከተረጋገጠ ለጽ/ቤቱ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) CPO ለውል ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችል መሆን ይኖርበታል። 
 22. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማብራሪያ፣ ማስተካከያ፣ ሃሳብ እና ጥያቄ ካለው ጨረታው ከመከፈቱ ከ5 ቀን በፊት ለጽ/ቤቱ ማቅረብ ያለበት መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል።እንዲሁም ጽ/ቤቱም በጨረታ ሰነዱ ላይ የማስተካከያ ወይም ማሻሻያ ሃሳብ ካለው ጨረታው ከመከፈቱ 5 ቀን በፊት ለተጫራቾች ማሳወቅ የሚችል መሆኑን መረዳት ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚቀርበው የማስተካከያ ሃሳብም ሆነ ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል። 
 23. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 
 • ማሳሰቢያ፡-ማንኛውም ተጫራች ድርጅት የሚወዳደርበትን መስፈርት በሙሉ በጥሞና አረጋግጦ መረዳት ይኖበታል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው ስህተት ምንም ዓይነት ማስተካከያ የማናካሂድ መሆናችንን እንገልፃለን። 
 • * ተጫራቾች ለጨረታ የሚሰጡት የመወዳደሪያ ዋጋ ከቫት በፊት እና ከቫት በኋላ መሆኑን በግልፅ የጨረታ ሰነዱ ላይ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል። 
 • አድራሻ፡- አዳማ ከተማ ከንግድ ምክር ቤት ፊት ለፊት 
 • ስልክ ቁጥር፡- 022-211-43-36 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ። 

የምስራቅ ሸዋ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት