Freight Transport / Transportation Service / Vehicle

የምስራቅ ሸዋ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለምስ/ሸዋ/ዞን ሕብረት ሥራ ኤጀንሲ የ2013/14 የምርት ዘመን ለመኸር ወቅት የሚውል የምርት ማሳደግያ ግብዓት ለመጓጓዣ የትራንስፖርት ባለንብረቶችን በግልጽ ጨረታ ለማወዳደር ይፈልጋል

2013/2014 የምርት ዘመን የምርት

ማሳደጊያ ግብዓት መጓጓዣ የወጣ

የጨረታ ማስታወቂያ

የምስራቅ ሸዋ  ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት ለምስ/ሸዋ/ዞን ሕብረት ሥራ ኤጀንሲ 2013/14 የምርት ዘመን ለመኸር ወቅት የሚውል የምርት ማሳደግያ ግብዓት ለመጓጓዣ የትራንስፖርት ባለንብረቶችን  በግልጽ ጨረታ ለማወዳደር ይፈልጋል፡፡

 ስለሆነም፡-

 1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የትራንስፖርት አገልግሎት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑ ግብር የከፈለበት መረጃ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች ከአሁን በፊት በዚህ ሥራ/ ተመሳሳይ ሥራ/ ቢያንስ 1(ኣንድ)  ዓመት ልምድ ያላቸውና እንዲሁም የስነምግባር ችግር የሌለባቸው ሆኖ ከዚህ በፊት በአገልግሎት አሰጣጣቸው ከተገልጋዮች ቅሬታ ያልቀረበባቸው እና ለሠሩት ሥራ ከሠሩበት ድርጅት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ መረጃው ከጨረታው ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
 3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ ሁለትመቶ/ በመክፈ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ  ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በምስራቅሸዋ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤትቢሮ ቁጥር 15 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ 2013. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ይዘው መምጣት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማዘጋጀት ቴክኒኩን ዋናውን እና ኮፒውን በተናጠል አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም . ተጫራች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሱን ዋናውን እና ኮፒውን በተናጠል ኣሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. የጨረታው አከፋፈት የሚካሄደው በቅድሚያ የቴክኒክ ኦርጅናል ሰነዱ ይከፈትና የቴክኒክ ግምገማ ውጤት እንዳለቀ የቴክኒኩን ግምገማ ያለፉ ተጫራቾች የፋይናንስ ኦርጅናል ሰነዳቸው የሚከፈት ሲሆን የቴክኒክ ግምገማውን ያላለፉ ተጫራቾች የፋይናንስ ሰነዳቸው ሳይከፈት የሚመለስላቸው ይሆናል፡፡
 7. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በግልጽ መፃፍ አለበት፡፡
 8. የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት 230 እስከ 1130 ይሸጥና ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ሰነዱ መሸጥ ከጀመረበት  ቀን ጀምሮ እስከ (16) አስራ ስድስተኛው የስራ ቀን እስከ 600 ሰዓት ድረስ ለጨረታው ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ 600 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ማለትም በአስራ ስድስተኛው (16)  የስራ ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት ተጫራቾች ወይም በጨረታው ላይ መካፈል የፈለጉ ማናቸውም ወኪሎቻቸው በተገኘበት ይከፈታል፡፡
 9. ተጫራቾች ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ / ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም የባንክ ጋራንት በዩኒየኑ ስም ለየብቻ ከጨረታው ሰነድ ጋር ያቀርባሉ፡፡
 10. በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚመዘገብ ማንኛውም ተወዳዳሪ  የጨረታው መጠናቀቂያ የመጨረሻው ዕለት ድረስ የጨረታ ዶኩሜንቱን ለመግዛት ጥያቄ አቅርቦ ባይፈቀድለት ለምስራቅ ሸዋ ዞን ሕብረት ሥራ ኤጀንሲ በስልክ ቁጥር 022-112-36-52 ቅሬታ ማቅረብ ይችላል፡፡
 11.  የጨረታው ኣሸናፊ ቀደም ሲል የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ/ ተመላሽ ሆኖ በአዲስ መልክ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር/ ለጨረታ አፈጻፀም ዋስትና በባንክ  በተረጋገጠ CPO እና ለእያንዳንዱ ለሚወዳደርበት ሎት/ዩኒየን የሁለት የጭነት መኪና ሊብሬ ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን የጨረታው ማስከበሪያው 100,000 /አንድ መቶ ሺህ/ ብር የሚመለሰው የጨረታ ስምምነት ማስከበሪያ 500,000 ሺህ አምስት መቶ ሺህ/ ገቢ ካደረገ በኋላ ነው፡፡
 12. የሚቀርበውን ብዛቱንና ወቅቱን ከግምት በማስገባት ለስራው  መቀላጠፍና በወቅቱ አርሶ አደር ጋር ለማድረስ ሲባል አንድ ተጫራች በሶስቱም ሎት/ዩኒየን ላይ መወዳደር ቢችልም ማሸነፍ የሚችለው ግን በአንድ ሎት(አንድ ዩኒየን) ላይ ብቻ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት  አንድ ተጫራች ከአንድ ሎት/ዩኒየን በላይ አሸናፊ ከሆነ አንዱን ሎት/ዩኒየን ብቻ መርጦ የሚወስድ ሲሆን ሌሎች ላይ የዞኑ ICU  ኮሚቴው እንዳስፈላጊነቱ የሚወሰን ይሆናል፡፡ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው አሸናፊ ከሆነ እና አሸናፊነቱ ከተገልጸለት በተዋዋለው ውል መሰረት በተባለው ቀን በተባለው ቦታ እና በተገለጸው ጊዜ  ማድረስ ካልቻለ ያሸነፈበት ስምምነት ላይ ማለትም ጠቅላላ ዋጋ ላይ 0.00% በየቀኑ ይቀጣል፡፡
 13. የምርት ማሳደጊያውን የሚያጓጉዘው መኪና ኢንሹራንስ መኖር አለበት።
 14. የምርት ማሳደጊያውን በመጓጓዝ ላይ እያለ ለሚያጋጥመው ችግርና በሚጠፋው ነገር ድርጅቱ ሙሉ በሙሉ ኃላፊነቱን ይወስዳል ፡፡
 15. ከዚህ በላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ሳይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈፅሙ ቢቀሩ በመንግስት ግዥ መመሪያ  ቁጥር 02/2004 እና FA 1/2009 እንዲሁም አዋጅ ቁጥር 157/2002 መሠረት /ቤቱ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል
 16. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማብራሪያ ፣ማስተካከያ፣ ሃሳብ እና ጥያቄ ካለው ጨረታው ከመከፈቱ 5(አምስት) ቀን በፊት ለጽ/ቤቱ በጽሁፍ ማቅረብ ያለበት መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል እንዲሁም  /ቤቱም በጨረታ ሰነዱ ላይ የማስተካከያ ወይም ማሻሻያ ሃሳብ ካለው ጨረታው ከመከፈቱ 5 ቀን በፊት ለተጫራቾች በመስታወቂያ ማሳወቅ የሚችል መሆኑን መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚቀርበው የማስተካከያ ሃሳብም ሆነ ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
 17. የዞኑ የምርት ማሳደጊያ ኮሚቴ የተሻለ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ አዳማ ከተማ ከንግድ ምክር ቤት ፊት ለፊት

ስልክ፡– 022- 111 – 99 -86/022-211-43-36 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡

 የምስራቅ ሸዋ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት