ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለ 2013 በጀት ዓመት ለፍርድ ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ
- የተለያዩ የፅዳት እቃዎች ፣
- የፅህፈት መሳሪያዎች እና
- የሰራተኞች ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጹት መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጨራቾች ይህንን ጨረታ እንድትካፈሉ ተጋብዘዋል።
- ተጨራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የንግድ መለያ (TIN Number)፤ ንግድ ምዝገባ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ማቅረብ የሚትችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ 4000.00(አራት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ(CPO) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00(ሃምሳ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 02 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ያሸነፈባቸውን እቃዎች አቅራቢው ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት ምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እቃ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ገቢ ያደርጋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ውጤት እንደ ታወቀ በጨረታ የተሸነፉት ተጫራቾች ወዲያውኑ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO ) ይመስላቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በግልፅ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ይሸጥና በ 16 (በአስራ ስድስተኛው) ቀን ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት ለተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ሰነዳቸውን ካስገቡ በኋላ ጨረታው በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል መጻፍ (መግለጽ) እና የድርጀታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለጸውን ማንኛውንም ሁኔታዎችን መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁኝ ማለት አይችልም።
- ማንኛውም ተጫራቾች የሚወዳደርበትን የእቃ ዓይነት ነጠላ ዋጋ ነው ማቅረብ ያለባቸው።
- ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በግልፅ መፃፍ አለበት።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ምርጫ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ ፡- አዳማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ከአርባ ሜትር መንገድ 200 ሜ. ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
- ስልክ ቁጥር 0221-12-26-53 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02
- ምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዳማ