ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ወረዳ እንሴኖ ከተማ በ2013 ዓ.ም በመደበኛና በካፒታል በጀት ዓመት በሎት ከፍለን ያቀረብናቸው እቃዎች ፤
- ሎት አንድ የጽህፈት መሳሪያ እና
- ሎት ሁለት የሞተር ሳይክል፧ ግዥ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡
በዚህም መሰረት፤
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፤ በዘርፉ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው በተጨማሪም የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የጨረታ ማስከበሪያ 10000 (አስር ሺህ ብር) ብቻ በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ በተናጠል ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፤ ፊርማቸውን ማስፈርና የድርጅታቸው ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ሰነዶችና ሌሎች ተፈላጊ መረጃዎች በኢንቨሎፕ በማሸግ 1 ኦርጅናል ቴክኒካል እና 1 ኦርጅናል ፋይናንሻል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በምስራቅ መስቃን ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ማ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁ-1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ላይ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5፡00 ሰዓት ላይ በምስራቅ መስቃን ወ/ፋ/ኢ/ል/ማ/ጽ/ቤት ግዥ ከፍል ላይ በይፋ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወኪሎቻቸው/ባይገኙም ጨረታው ከመክፈት አይታገድም፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ /የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር በመክፈል ምስራቅ መስቃን ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ማ/ጽ/ቤት ግዥ ክፍል ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- በመ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 0463-210158
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በጉራጌ ዞን
የምስራቅ መስቃን ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት