የጨረታ ማስታወቂያ
የምሥራቅ ወለጋ ዞን የጎቡ ሰዮ ወረዳ ገ/ኢ/ት ጽ/ቤት በ2013 በጀት ለወረዳው የሚውል
- የጽሕፈት መሣሪያ
- የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ
- የሕንፃ መሣሪያ
- የደንብ ልብስ
- ቦክሰር ሞተር እና
- ፈርንቸሮችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፤
በዚሁ መሰረት፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና አግባብ ያለውና የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር በመክፈል የ2013 ፍቃዳቸውን ያሳደሱ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የንግድ ፍቃዳቸውን ኮፒውንና ኦርጅናሉን እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT 15% ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ከመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ በኦሮሚያ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ 22/12 /2012 እስከ 8/1/ 2013 ዓ.ም ድረስ ሁልጊዜ በሥራ ሰዓት ጠዋት ከ2፡30 እስከ 6፡30 ከሰዓት በኋላ 7:30 እስከ 11:30 ሰዓት ከኦሮሚያ ገ/ኢ/ት/ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 304 3ኛ ፎቅ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የተፈለጉትን እቃዎች በዝርዝሩ መሰረት ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ እቃ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከብር 4000.00 እስከ 5,000.00 ብር በቼክ በተረጋገጠ በባንክ CPOማስያዝ አለባቸው፡፡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለተሸናፊዎች ወዲያው የሚመለስ ሲሆን የአሸናፊው ግን ውል እስኪፈረምና እቃውን እስኪያቀርብ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ጨረታው በ11/1 /2013 ዓ.ም ልክ በ 4፡00 ሰዓት ተዘግተው በዚያ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ቀኑ መ/ቤቱ ዝግ ከሆነ ወይም ዓመት በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ከተጫራቾች አሸናፊ የሆነው ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት በምሥራቅ ወለጋ ዞን የጎቡ ሰዮ ወረዳ ገ/ኢ/ት ጽ/ቤት ድረስ በማቅረብ ማስረከብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች አንዱ በአንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡በስልክ ቁጥር፡– 0917071659/0920421365 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
የቦታው ርቀት ከአ.አ እስከ አኖ ከተማ 266 ኪ.ሜ በዋናው አስፋልት ላይ ነው፡፡
የምሥራቅ ወለጋ ዞን የጎቡ ሰዮ ወረዳ
ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት