Building Construction / Contract Administration and Supervision

የማዕ/አር/ወረዳ ገ/ኢ/ት/ዋ/ጽ/ቤት በወረዳው አልማ ጽ/ቤት በጀት አንድ ብሎክ ባለ አራት መማሪያ ክፍል ግንባታ ጃንሱማ ከተማ ላይ እና አንድ ብሎክ ባለ አራት መማሪያ ክፍል ግንባታ ባንብል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በአጠቃላይ ሁለት ብሎክ እያንዳንዱ ባለ አራት መማሪያ ክፍል ለማስገንባት ይፈልጋል

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በማዕ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የማዕ/አር/ወረዳ /////ቤት 2013 በጀት አመት በወረዳው አልማ /ቤት በጀት አንድ ብሎክ ባለ አራት መማሪያ ክፍል ግንባታ ጃንሱማ ከተማ ላይ እና አንድ ብሎክ ባለ አራት መማሪያ ክፍል ግንባታ ባንብል አንደኛ ደረጃ /ቤት በአጠቃላይ ሁለት ብሎክ እያንዳንዱ ባለአራት መማሪያ ክፍል ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

 1. በዘመኑ የታደለ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
 2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
 4. የግንባታው መጠን ብር 200000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
 5. በግንባታ ስራ ነክ ተቋራጭ የተመዘገቡ በተሰጠው የስራ ዝርዝርና ፕላን መሰረት ሰርቶ ማስረከብ የሚችል ::
 6. ለግንባታው የሚያስፈልጉት የፋብሪካ ውጤት እና አጠቃላይ ለግንባታው የሚያስፈልጉ ግብአቶችን በራሱ አቅርቦት ማስገንባት የሚችል፡፡
 7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተቁ ከ1-6 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ለየብቻ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
 8. የግንባታውን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
 9. ከአሁን በፊት ወረዳዎችም ሆነ በሌላ ወረዳዎችም ግንባታ ለመስራት ውል ወስዶ በራሱ ችግር ያጓተተን አይጋብዝም፡፡
 10. ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በኢትዮጵያ አንድ መቶ (100) ብር ብቻ በመክፈል በማንኛውም ሰዓት 23/04/2013 . እስከ 14/05/2013 . በማዕ/አር ወረዳ /////ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 1130 በመምጣት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን እሁድ እና ቅዳሜ መንግስት በካላንደር የሚዘጋው በሚቀጥለው የስራ ቀን ተጫራቹ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ባይገኙም ለሚተላለፈው ህግ ተገዥ ይሆናሉ ፡፡
 11. የሚወዳደሩት ተወዳዳሪዎች ደረጃ ሰባት(7) እና ከዚያም በላይ መሆን አለባቸው እንዲሁም ስራውን በጥራት እና በብቃት መስራት የሚችል
 12. ጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋው 1% ማስያዝ የሚችል እና አሸናፊ ከሆነ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋው 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ በመ/ 1 ማስያዝ የሚችል፡፡
 13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 22ኛው ቀን 330 ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4:00 ሰዓት ይከፈታል ::
 14. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በተጫራቾች መመሪያ ወይም በስልክ ቁጥር 0918804213/0949573697 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአብክመ የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት

 /ማሰሮ ደንብ/