ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በ/አ/ብ/ክ/መ/በማዕ/ጎ/ዞን የማዕ/ኦር/ወ/ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለወረዳው ሴ/መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን
ማለትም፡
- ሎት 1 የፈርኒቸር ዕቃዎች
- ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት 3 የደንብ ልብስ
- ሎት 4 የግንባታ ዕቃዎች እነዚህን ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድር መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም:
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ያለው ፣
- ጠቅላላ የዕቃው ዋጋ 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከእዚያ በላይ ከሆነ የታጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ያለው መሆን አለበት፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተወዳዳሪዎች አጠቃላይ የጨረታ ሰነዱን ከማዕ/አር/ወ/ገ/ኢ/ል/ፅ/ቤት ቢሮ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በኢትዮጵያ 100.00 መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የዕቃውን 1% ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ የክፍየ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ በዋስትና ላይ ያልታመሰረተ ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡ እንዲሁም መስሪያ ቤቱ አሸናፊውን በሎት ይለያል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ዋናና ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመስሪያ ቤታችን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከ16/03/2013 እስከ 30/03/2013 ዓ.ም ለተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን፤ በአስራ ስድተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ እና 3:30 ላይ ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ባይገኙም ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቅዳሜ እና ዕሁድ ወይም መንግሥት በካላንደር የሚዘጋው ከሆነ በቀጣዩ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ዕቃዎችን ማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ማሰሮ ደንብ ማቅረብ የሚችሉ እና ከታዘዘው ዕቃ ውጪ ቢያመጡ በራሳቸው ወጪ እንዲመልሱ የሚደረግ እና ትክክለኛውን ዕቃ እንዲያቀርቡ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0918804213/ 0949573697 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
ማሳሰቢያ፡– ተቋሙ የተሻስ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ ቤት