ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡– ማስኤ/ግጨ/002-2013
መ/ቤታችን በ2013 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ግዥዎች ከመንግሥት በተፈቀደ መደበኛ በጀት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት መግለጫ |
የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና መጠን በብር |
1 |
ሎት፡-1 ልዩ ልዩ ሞዴል ያላቸው ፎቶ ኮፒዎች፣ የህትመት ማሽኖች፣ ኮምፒዩተሮች እና ፕሪንተሮች ቅድመ ብልሽት መከላከልና የብልሽት ጥገና አገልግሎት ግዥ፤ (ለሁለት ዓመት የሚቆይ ውል በመግባት) |
10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ |
2 |
ሎት፡-2 የተለያዩ ሞዴል ያላቸው የሊፍት ቅድመ ብልሽት መከላከል እና የብልሽት ጥገና አገልግሎት ግዥ፣ (ለሁለት ዓመት የሚቆይ ውል በመግባት) |
10,000.00/አስር ሺህ ብር/
|
3 |
ሎት፡-3 የመታወቂያ ካርድ ማተሚያ ማሽን / High End Enteprise ID printing Solution/ |
10,000.00/አስር ሺህ ብር/
|
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01 ከሚገኘው የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጄንሲ ዋና መ/ቤት ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመምጣት ለያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 100.00 /ብር አንድ መቶ/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ከግብር ዕዳ ነጻ ስለመሆናቸው ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ፤ በመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ ድረ–ገጽ www.pa.gov.et የተመዘገቡበትን ኮፒ፤ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሠርተፊኬት እንዲሁም የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገባበትን ቅጽ በመሙላት ፊርማና ማህተም በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
ለጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ የከፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በቅድመ–ሁኔታ ያልተገደበ የባንክ ዋስትና Central Statistics Agency ተብሎ የተዘጋጀ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ተያይዞ ያልቀረበ ወይም ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም::
ተጫራቾች የሚጫረቱበት በሎት በሎት2 እና በሎት3 ግዥ ለተጫራቾች በሚሸጠው የጨረታ ሰነዶች ከፍል 6 ላይ ከተመለከተው የቴክኒክ ፍላጎት መግለጫ ጋር መጣጣም ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ጨረታው በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከቀኑ 4፡30 ሰዓት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአዲሱ ህንጻ 2ኛፎቅ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል፡፡
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጀርባ
ስልክ ቁጥር/251-111118495
ሩክስ 251-11115470
የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ