የደን ሽያጭ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በምስ/ጎ/ዞን በማቻክል ወረዳ በአማሪ የወበሽ ቀበሌ ደጋ አማሪ ንኡስ ቀበሌ ልዩ ስሙ ደጋ አማሪ የሚባል ቦታ ላይ የሚገኘውን የለማ የማኅበረሰብ ደን /ዲከረንስ፣ ግራብሊያ/ እና በአማኑኤል ዙሪያ ቀበሌ የነጭ ንዑስ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጎጃም ዱር የሚባል ቦታ የሚገኘዉን
- የለማ የማህበረሰብ ደን/የፈረንጅ ጽድ/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- ለጨረታ የቀረበውን ደን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በተገለጸው ቦታ ድረስ በመሄድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ቀናት ማየት ይችላሉ።
- የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ ጨረታውን ባወጣው መ/ ቤት በመገኘት ብር 200 ብቻ ከፍሎ በስራ ቀናት መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የደን ዓይነት ለመግዛት የሞሉትን ዋጋ 10 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ,ፒ,ኦ/ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በአሃዝና በፊደል ምንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ በመጻፍ ማህተም በማድረግና በሰም በታሸገ ፖስታ በማሸግና በፖስታው ላይ ማህተም ስም አድራሻና የጽ/ቤቱን አድራሻ በመጻፍ በማቻክል ወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት ለዚሁ ተግባር ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር እስከ 20ኛው ቀን 11:00 ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል። ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ/ፊርማ/ መደረግ ይኖርበታል። ከሌለው ግን ከውድድር ውጪ ይሆናል።
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር በ20ኛው ቀን 11:00 ላይ ጨረታው ይዘጋል፣ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ላይ ይፈጸማል።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0587770220 ወይም 0913723509 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊው ድርጅት /ግለሰብ/ ሮያሊቲ ለመንግስት /13 በመቶ / ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከብር 200 ሺህ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የቫት ሰርተፊኬት /ቲን/ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት/ቲን/ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ፖስታዉን ሲያስገቡ የሁለቱን ቀበሌዎች በተለያየ ፖስታ በማሸግ ፖስታዉ ላይ የተወዳደሩበትን የእንጨት አይነት ለይቶ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
የማቻክል ወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት