የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የሚደጋ ቶላ ወረዳ ገንዘብና ትብብር ጽ/ቤት በወረዳችን ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤታችን የሚገዛ
- አላቂ የፅሕፈት መሳሪያ፤
- የፅዳት እቃዎች፣
- ኤሌክትሮኒክስ የቴክኒክና ሙያ እቃዎች፤
- የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፤ እና
- የደንብ ልብስ፤ እና
- ቋሚ እቃዎች እንዲሁም
- የመኪና እና፤ የሞተር ሳይክል፤ ጎማ፤ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህም የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- እቃዎችን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የ2013 ዓም. የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ
- ሀ.የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ለ. በገ/ኢ/ት/ሚኒስትር/ቢሮ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው የጨረታ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100፤ (አንድ መቶ) ብር በመክፈል ከሚደጋ ቶላ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት መግዛት የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊዎች ያሸነፉባቸውን እቃዎች ሙሉ በሙሉ በጨረታው ሰነድ ላይ በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ በራሳቸው ወጪ እስከ ወረዳው ገ/ኢ/ት/ፅ/ቤት መጋዘን የሚያቀርብ ቦታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ16ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ከቢሮ በሚሰጠው የእቃ ዝርዝር መሰረት ጨረታውን ከመከፈቱ 1(አንድ) ቀን በፊት የታዘዘውን የእቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251025-462-0037/38፣ 0932291204 ማነጋገር ይቻላል፡፡
የሚደጋ ቶላ ወረዳ ገንዘብና ትብብር ጽ/ቤት