የጨረታ ማስታወቂያ
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሚ/አ/ካ/ማዘጋጃ ቤት አገ/ት የሚውል
- ሞተር ሳይክል እና ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም
- ኤክስካቫተር ማሽን ፣ ግሬደር ማሽን ፣ ሲኖትራክ ገልባጭ መኪናና፣ ሎደር ማሽኖችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላል::
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የሥራ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ሙሉ ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 06 በመቅረብ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋቸውን ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሁለት ኮፒ እና ኣንድ ኦርጅናል በኣንድ ፖስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ማሳሰቢያ:- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በመሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 3360124
የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር
ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት