የጨረታ ማስታወቂያ
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል ከዚህ በታች የቀረቡትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የጤና ባለሙያ ደንብ ልብስ (በድጋሚ 2ኛ ዙር የወጣ)
- ሎት 2 የድጋፍ ሰጪ ሠራተኛ የደንብ ልብስ (በድጋሚ 2ኛ ዙር የወጣ)
- ሎት 3 የተሽከርካሪ ጎማና ባትሪ (በድጋሚ 2ኛ ዙር የወጣ)
- ሎት 4 የሰው ህክምና መድኃኒትና ላቦራቶሪ ሪኤጀንት (በድጋሚ 2ኛ ዙር የወጣ)
ስለሆነም ማንኛውም በዘርፉ አገልግሎት ሰጪ የተሰማሩ በውድድሩ ላይ እንዲካፈሉ እየጋበዝን በውድድሩ ላይ ለመካፈል ቀጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች ወይም መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀትና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ አለበለዚያ መ/ቤቱ የተሞላውን ዋጋ ከነቫቱ አድርጎ ነው የሚወስደው፡፡
- የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200 .00/ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል ከግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የፋይናንሻል መገምገሚያ መስፈርት መ/ቤቱ በሚያዘጋጀው በዋጋ ማቅረቢያ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በመሙላት ተፈርሞበት የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ ኦርጂናልና ኮፒውን ለብቻ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የቴክኒካል መገምገሚያ ሰነድ ለብቻው ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በማዘጋጀት ተፈርሞበት የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕፖስታ ኦርጂናልና ኮፒውን ለብቻ በማሸ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ናሙና ሳምፕል/ በዓይነት ከስፔስፊኬሽን ጋር በማድረግ በቴክኒካል ሠነድ ጋር መያያዝና መቅረብ ይኖርበታል፡፡ በየአንዳንዱ በሚቀርበው ናሙና ካታሎግ /ፎቶ ግራፍ ላይ የድርጅቱ ማህተምመደረግ አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ 30,000.00 ብር ሠላሳ ሺ ብር/ ለእያንዳንዱ ሎት በፖስታ ለብቻው ማሸግ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ይቆይና በ15ኛቀን 11፡00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን ዝግ ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው ድርጅት በግዥ ትዕዛዝ የሚሰጠውን ዕቃ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል (አማን ካምፓስ) መጋዘን ድረስ በራሱ ትራንስፖርትና ‘ወጪ የማጓጓዝና በራሱ የጉልበት ሠራተኛ የማስገባት ግዴታ አለበት፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በጽሑፍ ከተገለጸለት በኋላ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ለውል ማስከበሪያ የግዥውን 10% በባንክ በተመሰከረ CPO በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት። ውሉን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ባይገባ /ባይፈጸም/ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች እያንዳንዳቸው የሚወዳደሩበት ጨረታ የዕቃውን ዝርዝር በሠነዱ ላይ ያለውን ብቻ መሠረት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- . መ/ቤቱ የጨረታውን ግዥ 20% ከፍ ወይም ዝቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማሳሰቢያ፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- “አንድም እናት በወሊድ ምከንያት መሞት ያስባትም!! “
- አድራሻ፡- ሚዛን ቴፒ ዩንቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል
- ስልከ ቁጥር፡-0473360770
- የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል