ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው ዓይነት መደበኛ ጨረታ ቁጥር 1/2013
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/የሥራ ሂደት ለመ/ሜዳ ከተማ አስ ከንቲባ ጽ/ቤት G+2 የፎቅ ግንባታ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የግንባታ ማቴሪያል ግዥ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የግንባታ ማቴሪያሎቹን መግዛት ይፈልጋል፡፡
- የተለያየ መጠን ያለው የግንባታ ማቴሪያል አቅርቦት
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ያላቸው
- የግዥ መጠን ብር 200.000.00/ ሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም/VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- የሚገዙ የተለያየ መጠን ያለው የግንባታ ማቴሪያል አቅርቦት በወጣው የጨረታ ስፔስፊኬሽን መሰረት ከጨረታ ሰነዱ ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ እያንዳንዱ የተለያየ መጠን ያለው የግንባታ ማቴሪያል አቅርቦት 50/ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/የሥራ ሂደት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ቀን ድረስ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመምጣት በመግዛት ማግኘት ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ እያንዳንዱ ሎት የተለያየ መጠን ያለው የግንባታ ማቴሪያል አቅርቦት 3,000 / ሦስት ሺህ/ ብቻ cpo በመሂ 1 ወይም ከህጋዊ ባንክ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ልዩ ልዩ መረጃዎች ፎቶ ኮፒ አድርገው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/የሥራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 5 የተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ቀን ድረስ ሰነዱን በመገዛት ዋጋ ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በግ/ፋ/ን/አስ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 ጨረታው የሚከፈተው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ላይ ከቀኑ 7፡45 ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡00 ይከፈታል የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ተመሳሳይ ስዓት ታሽጎ ተመሳሳይ ቀን ይከፈታል፡፡
- ከላይ የተጠቀሰው ጨረታ አሸናፊው የሚለየው በተናጠል ወይም በድምር ሊሆን ይችላል የዋጋ አዋጭነቱ በግዥ ኮሚቴው እየተገመገመ የሚወሰን ይሆናል፡፡
- ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ለተደራጁ ማህበራት ካደራጃቸው ማህበራት የድጋፍ ደብዳቤ በማምጣትና ለሀገር ውስጥ ኩባንያዎች በመመሪያው መሰረት ልዩ ድጋፍ ይደረጋል/ኢንተርፕራይዙ በሚያመርተው ምርት ላይ ብቻ ሆኖ ሲገኝ ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡– 0116851529/0116851528 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/የሥራ ሂደት