በድጋሚ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው አይነት መደበኛ ጨረታ ቁጥር 4/2013
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በግ/ፋን/አስ/የስራ ሂደት ለመ/ሜዳ ከተማ አስ/ከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ጽ/ቤት 2013 በጀት ዓመት ለመሰረተ ልማት አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ የውሃ ዕቃዎች ግዥ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የንግድ ምዝገባ ሰርትፊኬት ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TlN/ ያላቸው
- የግዥ መጠን ብር 200,000.00/ ሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸው
- የሚገዙ የተለያዩ ልዩ ልዩ የውሃ ዕቃዎች አቅርቦት በወጣው የጨረታ ስፔስፊኬሽን መሰረት ከጨረታ ሰነዱ ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መግዥያ የማይመለስ የተለያዩ ልዩ ልዩ የውሃ ዕቃዎች አቅርቦት 100/ አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግ/ ፋ/ን/ /አስ/የሥራ ሂደት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ቀን ድረስ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመምጣት መግዛትና ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ የተለያዩልዩ ልዩ የውሃ ዕቃዎች አቅርቦት 20000 /ሃያ ሺህ / ብቻ CPO በመሂ1 ወይም ከህጋዊ ባንክ ማስያዝ አለባቸው። ልዩ ልዩ መረጃዎች ፎቶ ኮፒ አድርገው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/የሥራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 5 የተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ቀን ከቀኑ 7፡45 ድረስ ሰነዱን በመግዛት ዋጋ ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ወይም ባይገኙም ስግፋ/ን/አስ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተቆጥሮ 16 ቀን ላይ ከቀኑ 7፡45 ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡00 ይከፈታል። የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ተመሳሳይ ስዓት ታሽጎ ተመሳሳይ ቀን ይከፈታል፡፡
- ከላይ የተጠቀሰው ጨረታ አሸናፊው የሚለየው በተናጠል ወይም በድምር ሊሆን ይችላል። የዋጋ አዋጭነቱ በግዥ ገምጋሚ ኮሚቴው እየተገመገመ የሚወሰን ይሆናል፡፡
- ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ለተደራጁ ማህበራት ካደራጃቸው ማህበራት የድጋፍ ደብዳቤ በማምጣትና ለሃገር ውስጥ ኩባንያዎች በመመሪያው መሰረት ልዩ ድጋፍ ይደረጋል። /ኢንተርፕራይዙ በሚያመርተው ምርት ላይ ብቻ ሆኖ ሲገኝ፡፡
- የጨረታ ጊዜ ስአት ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ምንም አይነት ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይቻልም፡፡
- የቀረበው የዋጋ መወዳደሪያ ጨረታው ከተከፈተበት እለት አንስቶ ለ30 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0116851529/28 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት
ግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት