የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
የመድሐኒት አቅርቦት ኤጀንሲ /መአኤ/
ለሀገር ውስጥ አምራቾች የወጣ የሀገር ውስጥ የላብራቶሪ ኬሚካሎችና የህክምና መገልገያዎች የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው ቁጥር፡– NCB/PSA6/RDF-2013/MS/LR/04/20
በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ የሀገር ውስጥ የህክምና መገልገያዎችና ላብራቶሪ ኬሚካሎች አምራቾች ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሁሉ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች በመስኩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለበት።
- የጨረታው ተሳታፊዎች ከኢትዮጵያ የምግብ የመድሐኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣንን የማምረቻ ፈቃድ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ የማይመለስ ብር 100 መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸው ዋናውንና ሁለት ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ስምና አድራሻ እንዲሁም አስፈላጊ መረጃዎች በመጻፍ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱ ከታች በተገለፀው አድራሻ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ይሰጥና የመዝጊያው ሰዓት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ሲሆን የጨረታው መከፈቻ በተመሳሳይ ቀን 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
- በመጫረቻው ሰነድ ላይ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ተጫራቾች 500,000 ብር የጨረታ ማስከበሪያ ከኢንሹራንስ ተቋም ያልሆነ ወይም በምክንያት ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional bank guarantee) ወይም በሲፒኦ(CPO) በመጫረቻ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መጠን መሰረት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የመገምገሚያ መስፈርቱም በዝርዝር በመጫረቻ ሰነዱ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡
- ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ ያልተካተቱ ሕጎች በሀገራዊ ግዥ መመሪያው መሰረት ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡
አድራሻ፡– የመድሐኒት አቅርቦት ኤጀንሲ /መአኤ/ የጨረታ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከጳውሎስ ሆስፒታል ፊት ለፊት እዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ
ወረዳ 05 የፖስታ ሣጥን ቁጥር 21904
የስልክ ቁጥር +251 11 18 27 65 31
ፋክስ +251 11 275 25 55 አዲስ አበባ የመጫረቻ ሰነዱን ከላይ በተገለፀው
አድራሻ ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30-6፡30 ጠዋት እና ከ7፡30-11፡30 ከሰዓት በኋላ መግዛት ይቻላል፡፡
የመድሐኒት አቅርቦት ኤጀንሲ( መአኤ)