የጨረታ ቁጥር መአኤ 03/2013
የመድሐኒት አቅራቢ ኤጀንሲ/መ.አ.ኤ/ የሚከተሉትን ዕቃዎች በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፎቶ ኮፒና የፕሪንተር ቀለሞች፣አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣
- የተለያዩ የህትመት ውጤቶች፣
- የፈርኒቸርና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- የከፍተኛ ፣መካከለኛ ፣የፎር ክሊፍት እና የመስክ አውቶሞቢል ጎማዎች፣ ባትሪዎችና ፊልትሮዎች
- የስራ እና የደንብ ልብሶች ግዥ ጨረታ
- የቧንቧና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
ተጫራቾች፡
– በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ፣የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ለመሆናቸው የሚገልፅ ማስረጃ እና የግብር ከፋይነት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
– ተጫራቾች የጨረታውን መመሪያ ሰነድ ከጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
በጨረታው የሚሳተፉ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት (CPO) ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ሎት1፡– አላቂ የፅህፈት መሳሪያ፣የፎቶ ኮፒና የፕሪንተር ቀለሞችና የጽዳት ዕቃዎች ——60,000.00
- ሎት 2፡– የህትመት ውጤቶች——————- 50,000.00
- ሎት 3፡– የተለያዩ ፈርኒቸርና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች…….50,000.00
- ሎት4፦ የከፍተኛ፣መካከለኛ፣የፎርክሊፍት እና የመስክ አውቶሞቢል ጎማዎች ፣ ባትሪዎችና ፊልትሮዎች…100,000.00
- ሎት 5፡– የስራ እና የደንብ ልብሶች……………….60,000.00
- ሎት 6፡– የቧንቧና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ………………..50,000
ጨረታው ለሎት 1፣ 2 እና 3 ጥቅምት 23/2013 ዓ.ም የሚከፈት ሲሆን ሎት 4፣5 እና 6 ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል፡፡
ኤጀንሲው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይምበከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡– የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜድካል ኮሌጅ ፊት ለፊት
አዲስ አበባ
የስልክ ቁጥር፡-0112-765294
ፖ.ሳ.ቁ. 21904
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ