የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
የመካነ እየሱስ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 መሠረት በ2012 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር በመደበኛ ጨረታ ለመኖሪያ እና ለድርጅት አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ከ18/09/2012 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 250.00 ብር በመክፈል ቢሮ ቁጥር 07 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ መሸጥ ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በ3፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በከተማ አስተዳደር አዳራሽ ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ ወይም በስ.ቁጥር 058 447 07 07 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ቦታውን ለመጐብኘት የሚፈልግ አካል በ19/09/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ከተማ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 07 በመምጣት ከኮሚቴው ጋር በመገናኘት መጐብኘት ይቻላል፡፡
የመካነ እየሱስ ከተማ ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት