በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ጐንደር ዞን የመካነ ኢየሱስ/ከ/አስ/ገን/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት የተለያዩ ሎቶችን
- ሎት 1 የኤሌክትሪክ ዕቃዎች
- ሎት 2 የተዘጋጁ የደንብ ልብስ፣
- ሎት 3 የተዘጋጁ ጫማዎች እና
- ሎት 4 ብትን ጨርቅ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል::
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ::
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት የገንዘብ መጠን ከብር 200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 50 በመክፈል ከመ/ኢ/ከ/አስ/ገን/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 22 መግዛት ይችላሉ
- የዕቃውን ዝርዝር መግለጫዎች /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል
- ማንኛውም ተጫራች የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም ግብር ያካተተ መሆን ይኖርበታል
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደርበት ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስዝ አለባቸው
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱ ላይ እና ፖስታው ላይ የንግድ ድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለበት
- ማነኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ መ/ኢ/ከ/አስ/ገን/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 22 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ሎት 1, ሎት 2, ሎት 3 እና ሎት 4 ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል:: ማንኛውም ተጫራቾች በ16ኛው ቀን ጨረታ ሳጥኑ እስከ ሚዘጋበት ሰአት ድረስ ጨረታውን ማስገባት ይቻላል:: ለሁሉም ሎቶች ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው የሚከፈት ሲሆን የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም:: ጨረታው የሚከፈትበት ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም የካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል::
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም።
- ማንኛውም ተጫራች በዝርዝር ወይም በሎት ከቀረቡት ዕቃዎች ውስጥ ዋጋውን ነጥሎ መሙላት አይችልም:: ነጥሎ የሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል
- የጨረታ አሸናፊው እንደ ተቋሙ ፍላጐት በጥቅል ወይም በተናጠል ሊለይ ይችላል
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ በሙሉ በራሱ ወጭ በማጓጓዝ ከገዥው ተቋም ድረስ ማስገባት ይኖረበታል
- አሸናፊ ከሆነው ተጫራች ላይ 2 በመቶ ከተከፋይ ሂሳብ ግብር /ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ/ ተቀናሽ ይሆናል::
- አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ውሉን መፈፀም ይኖርበታል:: በተባለው ቀን መጥቶ ውሉን የማይፈጽም ከሆነ ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያው ለመንግስት ገቢ ይሆናል
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው:: ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 447 0121 እና 058 447 1022 ማግኘት ይችላሉ::
የመ/ኢየሱስ/ከ/አስ/ገን/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት