የመደበኛ ዕቃ ግዥ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ የስራ ማስኬጃ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- የተለያዩ የሠራተኞች እና
- የስፖርት አልባሳት፣
- የተለያዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና
- የትምህርት መርጃ መሳርያዎች፣
- የፅዳት ዕቃዎች እና
- ለህንፃ ለቁሳቁስ ዕድሳትና ጥገና (የቧንቧ ዕቃዎች)፣
- ለተለያዩ ፎቶ ኮፒ ማሽኖች ለዕድሳትና ጥገና የሚያገለግሉ መለዋወጫ ዕቃዎች፣
- ተጫራቾች ለወጣው ጨረታ በዚሁ የሥራ ዘርፍ የተስማሩ ስለመሆናቸው የሚረጋግጥ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት ወይም በመንግስት የግብር ህግ መሰረት ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) በመክፈል ከመከላከያ ዋር ኮሌጅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በመግዛት ዘወትር በስራ ሰዓት የሚወዳደሩበት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2% (ሁለት በመቶ) ለሚወዳደሩበት ዕቃ ማስያዝ ይኖርባችዋል።
- ጨረታው በ27/2/2013 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ መ/ክበብ ኣዳራሽ ይከፈታል።
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር -0113-6982 22
አድራሻ፡- ከመካኒሳ ከፍ ብሎ ቆሬ ካምፕ
በመከላከያ ሚኒስቴር
የመከላከያ ዋር ኮሌጅ