የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/JAN/O010/2013
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በሽጎሌ መኖሪያ አፓርትመንት (16-08B) ፕሮጀክት እና በስሩ ለሚሰራው የሰላም ማስከበር ህንፃ ግንባታ (20-03B) ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የሚገኙትን ዕቃዎች፤
- Lot 1. አሸዋ 1795 ሜኪዪብ የግንባታ ድንጋይ 165 ሜ.ኪዪብ ጠጠር 00 597 ሜ.ኪዪብ ጠጠር 02 1353 ሜ.ኪዪብ
- Lot2. Play Wood 122x244x1.8cm ብዛት 120 ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት::
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰአት ቅዳሜን ጨምሮ ተከታታይ 07 የስራ ቀናት ጃንሜዳ ስታፍ ኮሌጅ (17-06B) ፕሮጀክት የስታፍ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የፕሮጀክት ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ታህሳስ 30/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ታህሳስ 30/2013 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ከሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ፕሮጀክቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡– የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የጃንሜዳ አዣዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ፕሮጀክት (17-06B)
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0118-95-98-10 ወይም 0118121352