የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/BM/124/2020
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለጣርማበር–ሞላሌ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Galvanized pipe ከዚህ በታች በሰንጠረዡ በተገለፀው የሥራ ዝርዝር (Specification) መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
No |
Description |
Unit
|
Qty
|
1 |
Galvanized Pipe (3 inch)
|
PCS
|
200
|
ስለሆነም፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፣ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችላቸው የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ኦርጅናል ወይም የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት ኮፒ ካታሎግ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ወይም በጨረታ መክፈቻ ቀን በካታሎጉ ላይ የሚወዳደሩበትን ዕቃ ለይቶ በማመልከት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በአንድ ሞዴል ብቻ ነው። በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ናሙና ከጨረታው መክፈቻ ሰዓት በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ናሙና ያላቀረቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሠፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መ/ቤት የግዥ የሥራ ሂደት ኬዝ ቲም ሲሮ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታው ለተዘረዘሩት ዕቃዎች ብዛት (Quantity) በሙሉ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34/33
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
ኦ.ሳ.ቁ 3414
ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46
ወሱ ሰፈር የቀድሞው ኖሬሳ ግቢ
Email:- Info@dce-et.com