የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- DCE/EM/115/2020
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለድሬዳዋ አፓርትመንት ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በተገለፀው የሥራ ዝርዝር መሰረት የ Compound light fitting and Compound Pole ግዥ ለመፈጸም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
No |
Description |
Unit |
Qty |
|
External Light fittings And Lamps |
|
|
|
Specified or Equivalent approved) |
|
|
1 |
Compoound light fitting type beppe 400 E-27 BASE CAPE AND 50 LED lamp or approved equivalent |
No |
48 |
2 |
3.0m hot dip galvanized steel pole after fabrication covered by resin, black as manufactured by Fumagalli or approved equivalent flange mounted including fuse box, fuse, anchor bolt and all other accessory |
No |
48 |
ስለሆነም፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ፣ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መ/ቤት የግዥ የሥራ ሂደት ኬዝ ቲም ቢሮ መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ኦርጅናል ወይም የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት ኮፒ ካታሎግ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ወይም በጨረታ መክፈቻ ቀን በካታሎጉ ላይ የሚወዳደሩበትን ዕቃ ለይቶ በማመለከት ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: እንዲሁም በቴክኒክ ሰነድ ማጠቃለያ ሠንጠረዥ ላይ ሚወዳደሩበት ማቴሪያል የሚያቀርቡት ዕቃ ተመጣጣኝ ወይም (Equivalent) ከሆነ በግልፅ ተለይቶ መቀመጥ ይኖርበታል:: ናሙናን በተመለከተ ባቀረቡት ካታሎግ መሠረት እና በዋጋቸው የሚመረጡ ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡ ሲየጠቁ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው:: ሆኖም ከላይ መሟላት እንዳለበት ከተጠቀሱት ነጥቦች አንዱም ቢጐድል ተጫራቹ ቴክኒካል መስፈርቱን እንዳላሟላ ተቆጥሮ ሠነዱ ተመላሽ ይደረግለታል::
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች በተጠቀሰው ብዛት (Quantity) መሠረት መሆን ይኖርበታል::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ነሐሴ 05 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ነሐሴ 05 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 8፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34/33 ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
ፖሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46 ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
www.dce.et.com/ E-mail info@dce-et.com